loading
ለመጀመሪያ ጊዜ በበይነ መረብ ለማስተማር ለ4 ተቋማት ፈቃድ ተሰጠ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2013  በበይነ መረብ (ኦንላይን) ትምህርት ለመጀመር ካመለከቱ 9 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ ለ4 ተቋማት የእውቅና ፈቃድ መስጠቱን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታወቀ። በዚህም አራቱ ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪና በሁለተኛ ዲግሪ በ6 ፕሮግራሞች የእውቅና ፈቃድ እንደተሰጣቸው ነው የኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ገረሱ ለኢቲቪ የገለጹት።

በበይነ መረብ (ኦንላይን) ለማስተማር ፈቃድ ያገኙት ያርድስቲክ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ፣ ኢቲ ኦንላይን ኮሌጅ፣ ኤስቲ አሜሪካን ኮሌጅ ኦፍ ቴክኖሎጂ እና ላይትማፕ ኮሌጅ ናቸው። ከዚህ በፊት በመንግስትም ይሁን በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የበይነ መረብ (ኦንላይን) ትምህርት መመሪያ አለመኖሩን የገለጹት ዳይሬክተሩ አሁን ግን መመሪያው ተግባራዊ ተደርጎ ትምህርት በበይነ መረብ እንዲጀመር አድርገናል ነው ያሉት። ከዚህ በተጨማሪም ኤጀንሲው ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኢንፎርሜሽን ማኔጅመንት ሲስተም በልጽጓል ያሉት ዳይሬክተሩ የ257 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃ ወደ
መረጃ አስተዳደር ሲስተም ገብቷል ብለዋል። በዚህ ሂደት የ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ተማሪዎች እና ምሩቃን መረጃ እና 2ሺህ 750 ፕሮግራሞች ወደ
ሥርዓቱ ገብቷል ብለዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *