loading
ለሴቶች ከፍ ያለ ደረጃ መድረስ ከትምህርት ሌላ ምንም መሰላል እንደሌለ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 29፣ 2013 ለሴቶች ከፍ ያለ ደረጃ መድረስ ከትምህርት ሌላ ምንም መሰላል እንደሌለ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ ፡፡ ሴቶች በትምህርታቸው ውጤታማ በመሆን ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎችን በብቃት መምራት እንደሚችሉ አምነው እንዲማሩ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መክረዋል።ፕሬዚዳንቷ  ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ የቱሉ ዲምቱ ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው ከትምህርት ቤቱ የስርዓተ ጾታ ክበብ አባላት ጋር የተወያዩ ሲሆን ፤የሴት ተማሪዎች የትምህርት  ተሳትፎ፣ ከትምህርት ቤቱ ማኅበረሰብ የሚደረግላቸው እገዛናያሉባቸውን ክፍተቶች ለፕሬዚዳንቷ ገልፀውላቸዋል።ሴት ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፏቸው ውጤታማ መሆኑን በመግለጽ የንጽህና መጠበቂያ አቅርቦትና  የመቀየሪያ ክፍል ችግር እንዳለባቸውም አመልክተዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚደረጉ ድጋፎችን፣  የስርዓተ ጾታ ክበብ በማቋቋም ችግሮቻቸውን ለመፍታት የሚደረገውን ጥረትና ሌሎች አገል ግሎቶች በትምህርት ቤቱ መደራጀታቸውን በጉብኝታቸው ማረጋገጣቸውን  ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ለሴቶች በሰጠችው ትኩረት በከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎች እያገለገሉ እንደሚገኙ ጠቅሰው ይህም  ሴቶች እድል ካገኙ እንደሚችሉ ማሳያ በመሆኑ ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው እንዲበረቱ መክረዋል። ከትምህርት ሌላ ወደ ላይ ለመውጣት ምንም መሰላል የለም ያሉት ፕሬዚዳንቷ ጥረት፣ ትጋት፣ ተወ
ዳዳሪነት፣ በራስ መተማመን አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል።

ዕድሉን አግኝተው ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ ላይ የደረሱ ሴቶች ከታች ያሉትን መደገፍና ማበረታታት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።ሴቶች  ለእኩልነት ያደረጉትን ትግል የሚዘክረው ዓለም አቀፉ የሴቶች  ቀን /ማርች 8/ በኢትዮጵያ ለ44ኛ ጊዜ ተከበሮ ዉሏል ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *