loading
ለአንጋፋው ፊልም ሰሪ ኃይሌ ገሪማ ሽልማት ተበረከተላቸው::

ለአንጋፋው ፊልም ሰሪ ኃይሌ ገሪማ ሽልማት ተበረከተላቸው::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014  የኦስካርን ሽልማት በመስጠት የሚታወቀው ዘ አካዳሚ ኦፍ ሞሺን ፒክቸር አርትስ ኤንድ ሳይንስስ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን ሙዝየም መክፈቻን አስመልክቶ ከፍተኛ ሽልማቱን ለአንጋፋው ፊልም ሰሪ
ኃይሌ ገሪማ አበረከተ። በጥቁሮች የሲኒማ ታሪክ ላይ ከፍተኛ ስፍራ ያላቸው ኢትዮጵያዊው ኃይሌ ገሪማ ዘ አካዳሚ ሙዝየም
ኦፍ ሞሺን ፒክቸርስ የቫንቴጅ ሽልማት የመጀመሪያው ተሸላሚ ሆነዋል።

እንደ ሳንኮፋ እና አሽስ ኤንድ ኤምበርስ ከሚባሉ ምርጥ ፊልሞች በስተጀርባ ያሉት አንጋፋው የፊልም ዳይሬክተር ኃይሌ የሎስ አንጀለሱ ሙዝየም መክፈቻን አስመልክቶ ቅዳሜ ዕለት ባደረገው ሥነ ሥርዓት ላይ ነው ሸልማቱን እንደሰጣቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ኢትዮጵያዊው ኃይሌ ገሪማ ቫንቴጅ የተባለውን ሽልማት የተሸለሙበትን ምክንያት አስመልክቶ ሙዝየሙ እንዳስታወቀው በሲኒማ ዙሪያ ዋነኛ ትርክቶችን በመገዳደርና አውድ በማስያዝ የረዳ አርቲስትና ምሁር በሚል እንዳከበራቸው አስታውቋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *