
ለኢህአዴግ ጉባዔ በሀዋሳ ዝግጅቱ ተጠናቋል
አርትስ 22/01/2011
ነገ ጠዋት” አገራዊ አንድነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ለሚጀመረው 11ኛው የኢህዴግ ጉባዔ በቂ ዝግጅት መደረጉን የገለፁት አቶ ፍቃዱ ተሰማ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚና የጉባዔው አዘጋጅ ኮሚቴ ናቸው።
በመጪዎቹ 3 ቀናት ከሚወያይባቸው ጉዳዮች መካከል በ10ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎች እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ይወያያል። በጉባዔው ላይ ከ 2ሺህ በላይ ሰው ሲሳተፍ 1ሺዎቹ በድምፅ የሚሳተፉ ሲሆን ቀሪዎቹ እንግዶች ናቸው።