loading
ለኮሮና ቫይረስ መከላከል ድጋፍ የሚውል ከ500 ሺህ በላይ ማስክና የገንዘብ ድጋፍ ተበረከተ።

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2012 ለኮሮና ቫይረስ መከላከል ድጋፍ የሚውል ከ500 ሺህ በላይ ማስክና የገንዘብ ድጋፍ ተበረከተ።
በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ከ6 የቻይና ተቋማት የተሰባሰቡ 500 ሺህ ማስኮችና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለከተማ አስተዳደሩ አበርክተዋል።
የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ተቋማትም 1ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በተጨማሪም 180 ሺህ ብር የሚገመት በእግር የሚሰራ እጅ መታጠቢያ ድጋፍ ተደርጓል።

ድጋፉን የተረከቡት ኢ/ር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ አስቸጋሪ ወቅቶች ቢከሰቱ በሚል በየአካባቢው ነዋሪዎች የተዋቀረ የብሎክ አደረጃጀት በመፍጠር እንዲሁም የምግብ ባንክ በማዘጋጀት ዝግጅት እንዳደረገ ተናግረዋል።ለዚህም ከተለያዩ ዜጎች የሚደረጉ ያልተቋረጡ ድጋፎች ወሳኝ መሆናቸውን ጠቁመው ህብረተሰቡ በቻለው መልኩ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።በድጋፍ የተገኙት ማስኮች ለመንግሥት ሠራተኞች፣ለጤና ባለሙያዎች እና ለፖሊሶች እንደሚከፋፈሉ ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *