ለኮቪድ 19 ህሙማን እና አገልግሎት ሰጪዎች የእራት ግብዣ ተደረገ::
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 ለኮቪድ 19 ህሙማን እና አገልግሎት ሰጪዎች የእራት ግብዣ ተደረገ::በሚሊኒየም አዳራሽ የኮቪድ ማዕከል ለሚገኙ ቁጥራቸው አንድ ሺ ለሚሆኑ ሰዎች የአዲስ አመትን በዓል ምክንያት በማድረግ የእራት ግብዣ መደረጉ ተሰምቷል፡፡
በእራት ፕሮግራሙ 3 መቶ ለሚሆኑ የኮቪድ 19 ታማሚዎች ባሉበት ሆነው መመገብ ይችሉ ዘንድ ምግብ የቀረበላቸው ሲሆን ቁጥራቸው 7 መቶ ለሚሆኑት ሃኪሞች እና የተለያዩ አገልግሎተ ሰጪ ባለሙያዎች ደግሞ በቤስት ዌስት ፕላስ ሆቴል የቡፌ አገልግሎት እንደተደረገላቸው የሆቴሉ ጀነራል ማናጀር ሚስተር ኢቫን ሉዋን ነግረውናል፡፡
የአዲስ አመት በዓልን ምክንያት በማድረግ በቢስት ዊስት ፕላስ ሆቴል አዘጋጅነት የተደረገው የእራት ፕሮግራም በገንዘብ ሲለካ ከአምስት መቶ ሺ ብር በላይ የሚተመን ሲሆን በዚህም በማቆያ ማዕከሉ የሚገኙ ህሙማንን ጨምሮ ሌሎች ባለሙያዎችን ለማበረታታት ያለመ መሆኑየሬስቶራንት ማናጀር አቶ ይርጋ ቢረዳ ገልፀዋል ::ቢስት ዊስት ፕላስ ሆቴል ከሶስት አመት በፊት በኢትዮጵያ ሆቴል ኢንዱስትሪውን በመቀላቀል አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ሰምተናል::