loading
ለጋሞ አባቶች እውቅና የመስጠት ስነስርአት ተካሄደ
አርትስ 10/03/2011
በአርባምንጭ ከተማ ጠብን በሳር ለመለሱ የጋሞ አባቶች
በዚህ አመት ለ10ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአባቶች ቀን ምክንያት በማድረግ በዱም ሚድያ እና ኮምንኬሽን አዘጋጅነት ነው ዕውቅዉ የተሰጠው።
የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪ ወጣት እዮብ አርጋው ለአርትስ ቲቪ እንደተናገረው ድርጅቱ ላለፉት ዘጠኝ አመታት የአባቶች ቀን በማስመልከት በተለያዩ ዘርፎች ለሀገር እና ለትውልድ ምሳሌ ለሚሆኑ 180 አባቶች ዕውቅና ሠጥቷል ።
የጋሞ አባቶች ደግሞ ባህላዊ እሴቶችን ጠብ ለማስቆም እና ዕርቅ ለማውረድ ተጠቅመዋል ብሏል።
እውቅና ያገኙት አባቶች በበኩላቸው ባህላዊ እሴቶች እንዳይጠፉ ወጣቱን ያሳተፈ መድረክ መዘጋጀቱን አድንቀው ሰዎች በጋራ በሚሩበት ወቅት በርካታ ነገሮች ስለሚያተሳስራቸው አለመግባባት ይፈጠራል አለመግባባትን ግን በሰከነ መንገድ መፍታት ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት የኖሩበት እሴት ነው ብለዋል።
በዝግጅቱ ላይ ለእነዚህ አባቶች እግር የማጠብ ጋቢ የማልበስ እና የዕውቅና ወረቀት የመስጠት ስነስርአት መካሄዱን ተመልክተናል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *