loading
ሉሲዎቹ የኦሊምፒክ ማጣርያዋን ከዩጋንዳ ጋር ታደርጋለች

ሉሲዎቹ የኦሊምፒክ ማጣርያዋን ከዩጋንዳ ጋር ታደርጋለች

 

 

በጃፓኗ መዲና ቶኪዮ የሚከናወነው የ2020 ኦሊምፒክ ላይ በሴቶች እግርኳስ ለመሳተፍ የሚደረጉ የማጣርያ ጨዋታዎች በቀጣይ ዓመት መጀመርያ እንደሚከናወኑ ታውቋል።

 

 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ዋና ፀኃፊ አቶ ሰለሞን ገብረሥላሴ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የመጀመርያ የውድድር ዘመን አጋማሽ ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታዋን ከዩጋንዳ ጋር የምታከናውን ሲሆን ከኖቬምበር 4-12 (ህዳር 2012) በሚደረገው የደርሶ መልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ የመጀመርያ ጨዋታዋን በሜዳዋ እንደምታደርግ ተናግረዋል።

 

ኢትዮጵያ ይህንን ዙር የምታልፍ ከሆነ በቀጣይ ከካሜሩን ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር እንደምትጫወትም ተገልጿል።

 

 

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሪዮ 2016 ማጣርያ ላይ ያልተሳተፈ ሲሆን በለንደን የ2012 ኦሊምፒክ፤ በዲ.ሪ ኮንጎ 3-0 ድምር ውጤት ተሸንፎ ከመጀመርያው ዙር ተሰናብቷል።

 

 

ምንጭ፡ ሶከር ኢትዮጵያ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *