loading
ሊቢያ በሉዓላዊነቴ ጣልቃ የሚገቡ ሀገራትን አላስቆመልኝም ስትል የመንግስታቱን ድርጅት ወቀሰች::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ23፣ 2012  ሊቢያ በሉዓላዊነቴ ጣልቃ የሚገቡ ሀገራትን አላስቆመልኝም ስትል የመንግስታቱን ድርጅት ወቀሰች:: በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊቢያ ልዑክ ጣሂር አል ሱኒ በተለይ ግብፅ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በሀገራችን የውስጥ ጉዳያችን በግልፅ ጣልቃ ሲገቡ ዝም ብሎ መመልከቱ ትክክል አይደለም ሲሉ ደርጅቱን ወቅሰዋል፡፡ ልዩ ልዑኩ ይህን ያሉት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው፡፡ ሀገራቱ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እውቅና ያለውን መንግስት ለመጣል የሚንቀሳቀሰውን የጄኔራል ከሊፋ ሀፍታርን ጦር እንደሚደግፉ እየታወቀ ለምን ለማስቆም እንዳልተሞከረ ግልፅ አይደለም ብለዋል አምባሳደር አል ሱኒ፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ግብፅ በቅርቡ በምስራቃዊ ሊቢያ የሚንቀሳቀሰውን የሃፍታር ጦር ጥያቄ በመቀበል ጦሯን በሊቢያ ለማሰማራት በፓርላማ ማፅደቋ የሊቢያን መንግስት አስቆጥቷል፡፡ አል ሱኒ በተለይ ዓለም አቀፍ ህግን በሚጥሱ ሀገራት ማእቀብ እንዲጣልባቸው እንዲያጣራ የተቋቋመው ኮሚቴ ስራውን በአግባቡ እየሰራ አይደለም፣ ይህ ቢሆን ኖሮ እኛ ላይ ጣልቃ የሚገቡ
ሀገራት እርምጃው በተወሰደባቸው ነበር ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *