loading
ላውረን ባግቦ ወደ ሀገራቸው ሲገቡ ፕሬዚዳንታዊ አቀባበል ሊደረግላቸው መሆኑ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8፣ 2013  የቀድሞው የኮትዲቯር ፕሬዚዳንት ላውረን ባግቦ ከአስር ዓመት ስደት በኋላ በመጭው ሀሙስ ወደ ሀገራቸው እንደሚገቡ የፓርቲያቸው ዋና ፀሃፊ ተናግረዋል፡፡ በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ፓርቲያቸው ፖፑላር ፍሮንት በሰጠው መግለጫ ባግቦ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ በቪአይፒ ክፍል እንዲያርፉ ተደርጎ ፕሬዚዳንታዊ የክብር አቀባበል ይደረግላቸዋል ብሏል፡፡

የቀድሞ ተቀናቃኛቸውና የወቅቱ ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ባግቦ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው መልካም ነው ብለዋል፡፡ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶባቸው ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ ነጻ የወጡት ባግቦ ከገዥው መንግስት ጋር በድርድር ከተስማሙ በኋላ ነው ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የወሰኑት፡፡
እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2010 በተደረገው ባግቦና ኦታራ በውጤቱ ባለመስማማታቸው በሀገሪቱ በተቀሰቀሰው ግጭት 3 ሺህ ሰዎች ህይዎታቸውን አጥተዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ኦታራ ለሶስተኛ ጊዜ በምርጫ እወዳደራለሁ ማለታቸውን ተከትሎ ኢህገ መንግስታዊ ነው በሚል በሀገሬው ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ተነስቶባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *