loading
ልዩነትን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት ለሀገር ሠላምና ዘላቂ ልማት መቆም እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ፡፡

ልዩነትን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት ለሀገር ሠላምና ዘላቂ ልማት መቆም እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር  አቶ ደመቀ መኮነን በባህር ዳር “የጋራ ራዕይና ግብ ለአማራ ሕዝብ ዘለቄታዊ አንድነትና ሁለንተናዊ ስኬት” በሚል መሪ ሐሳብ  በተካሄደዉ ጉባኤ ላይ አንደተናገሩት የታፈረች ሀገር መመሥረት የሚቻለው በትንንሽ አጀንዳዎች ላይ ጊዜን በማጥፋት ሳይሆን ትላልቅ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት  ነዉ ብለዋል፡፡ሚኒስትሩ በተጨማሪም ሌሎች ባዘጋጁት አጀንዳ ከመጠላለፍ በመውጣት በአንድነትና አብሮነት በሀገራዊ ግንባታ ላይ መጓዝ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ በበኩላቸው ጉባኤው በክልሉ ያጋጠሙትን ችግሮች በማረም ወደ ቀደመው ሠላምና ፍቅር ለመጓዝ ያስችላል ብለዋል።የአማራ ብዙሀን መገኛና ድርጅት  እንደዘገብው በየደረጃው የሚገኙ መሪዎችም ለራስ ክብር ከመጨነቅ ወጥተው ለክልሉ ሕዝብ ችግሮች የመፍትሔ አካል መሆን አንዳለባቸው በመደረኩ ተገልጿል፡፡በተጨማሪም ምሁራንም ከዳር ተመልካችነት ወጥተው በምክንያታዊና ሳይንሳዊ ትንተና በማቅረብ ምሁራዊ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል ተብሏል፡፡እንዲሁም የሚዲያ አካላት ሚዛናዊ፣ ተዓማኒነት ያለው፣ ዴሞክራሲን የሚያጎለብት ዘገባ ለማኅበረሰቡ እንዲያቀርቡ ተጠይቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *