loading
ሐሰት፡ ይህ ምስል በኢትዮጵያ እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም።

ምስሉ የተወሰደው አዶቤ ስቶክ ከተሰኘ የምስል መገበያያ ድረ-ገጽ ላይ ነው።

ልጥፉ ላይ “ደሴ ባለስልጣኖች ያረፉበት ሆቴል በጁንታው ተመታ” የሚለው ጽሁፍ ሐሰተኛ ነው።

ይህ የፌስ ቡክ ልጥፍ “ደሴ ባለስልጣኖች ያረፉበት ሆቴል በጁንታው ተመታ ! የመከላከያ ጀነራል ሞተ።አሁን ከደሴ አሳዛኝ መረጃ” ይላል።

የያንዴክስ የምስል ፍለጋ (Yandex image search) እና የቲንአይ የምስል ፍለጋ (tineye image search) የጥምር ውጤት እንደሚያሳየው ትክክለኛው ምስል በኤደን የመን  አል-ጃላ ካምፕ ላይ የደረሰ የባለስቲክ ሚሳኤል ጥቃትን ያሳያል።

ምስሉ እ.ኤ.አ ሀምሌ 2019 ዓ.ም በኤደን፣ የመን በአል-ጃላ ካምፕ ላይ አዲስ ምልምል ወታደሮች በምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ እያሉ በደረሰ የባሊስቲክ ሚሳኤል ጥቃት የተጎዱ ወታደሮች መሬት ላይ ተኝተው ያሳያል።

በደሴ ከተማ አቅራቢያ ባሉ ስፍራዎች በመንግሥት ኃይሎችና በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ታጣቂዎች መካከል ከባድ ውጊያ የተካሄደ ሲሆን ከደሴ ከተማ ውጪ ከሚገኝ ስፍራ በህወሓት ኃይሎች በከተማዋ ላይ በተፈጸመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት በሰዎች ላይ ሞትና የመቁሰል ጉዳት ደርሷል።

ይሁንና በደሴ ከተማ ባለስልጣኖች ባረፉበት ሆቴል ከህወሀት አማጺ ጥቃት ስለመሰንዘሩ ከታማኝ ምንጭ የተዘገበ ዘገባ የለም

አርትስ ቲቪ ባደረገው ማጣራት ”ደሴ ባለስልጣኖች ያረፉበት ሆቴል በጁንታው ተመታ” በሚል የተለጠፈውን የፌስቡክ ልጥፍ ተመልክቶ ሐሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

.           .            .           .            .

ይህ ልጥፍ በፌስቡክ እና በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የፔሳቼክ የእውነታ መርማሪዎች በተከታታይ የሚያደርጉት የመረጃ ማረጋገጥ እና የተሳሳተ መረጃን የማጋለጥ ተግባር አካል ነው::

እንደ ፔሳቼክ ያሉ ገለልተኛ ሶስተኛ ወገን የእውነት መርማሪ ድርጅቶች ከፌስቡክ እና የማህበራዊ ድረ ገጾች ጋር በመጣመር የሃሰት ዜናን መለየት እንዲያስችልዎ ይሰራሉ:: ይህን የምናደርገውም በየማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የሚመለከቱት ልጥፍ/ መረጃ መነሻቸውን በማያያዝ እና ጠለቅ ያለ ዕይታ እንዲኖርዎ በማድረግ ነው::

በፌስ ቡክ ላይ የሐሰተኛ መረጃ ወይም የተጭበረበረ የመሰልዎ አጋጣሚ አለ?እንግድያውስ በእዚህ መንገድ ጥቆማ መስጠት ይችላሉ::እንዲሁም ይህን ተጨማሪ ኢንፎርሜሽን በመጠቀም አጠራጣሪ መልዕክቶችን ለመለየት የፔሳቼክ መንገዶችን ማየት ይችላሉ::

https://miro.medium.com/max/400/0*w5yMtCGA1dJdWsaN

ይህ የእውነታ ምርመራ በአርትስ ቲቪ የእውነት መርማሪ ረደኤት አበራ ተጽፎ በፔሳቼክ /አዘጋጅ ኤደን ብርሃኔ አርትኦት የቀረበ ነው::

አንቀጹ ለህትመት እንዲበቃ ያረጋገጠው ደግሞ የፔሳቼክ /አዘጋጅ ኤኖክ ናያርኪ ነው::

https://miro.medium.com/max/394/0*W96t_rnxwPEV6GVv

ፔሳቼክ የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የፋይናንስ መረጃ መርማሪ ተቋም ነው :: ካትሪን ጊቼሩ እና ጀስቲን አርንስቴን በተባሉ ሰዎች የተመሰረተ እንዲሁም በአህጉሪቱ ትልቁ የሲቪክ ቴክኖሎጂ እና የጋዜጠኝነት መረጃ ቋት አቅራቢ በኮድ አፍሪካ የተገነባ ነው:: እንደ ጤና : የገጠር ልማት እና የንጹህ ውሃ አቅርቦት በመሳሰሉ መስኮች ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ከመንግስት የሚጠበቁ አቅርቦቶች ላይ የተጨባጩን ዓለም እይታችንን ሊቀርጹ የሚችሉ በይፋ በሚሰራጩ የፋይናንንስ መረጃዎችን ዙርያ ህብረተሰቡ እውነተኛ መረጃን ማገናዘብ እንዲችል ለማገዝ የሚያስችል ድጋፍ ይሰጣል:: ፔሳቼክ ሚድያዎች የሚያቀርቡትን ጥንቅርም ይፈትናል:: የበለጠ መረጃ ለማግኘት pesacheck.org. ይጎብኙ::

https://miro.medium.com/max/60/0*YkqT49Yqdeot06Pp?q=20
https://miro.medium.com/max/70/0*YkqT49Yqdeot06Pp

Follow Us

https://miro.medium.com/max/54/0*mDTpdvUOWw1Vdz82?q=20
https://miro.medium.com/max/61/0*mDTpdvUOWw1Vdz82

Like Us

https://miro.medium.com/max/60/0*3pOdHCEnn3ovvbS_?q=20
https://miro.medium.com/max/72/0*3pOdHCEnn3ovvbS_

Email Us

ፔሳቼክ ኮድ ፎር አፍሪካ ከዶቼቬለ አካዳሚያ ባገኘው ድጋፍ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሚድያዎች እንዲሁም የሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር ኢኖቬት አፍሪካ ፈንድ በሚለው መስመሩ የሚያቀርበው እንቅስቃሴ ነው::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *