loading
ሐሰት፡ ይህ ምስል የህወሓት አማጽያን አንዋጋም ያሉትን ወጣቶች ሲረሽኑ አያሳይም።

ምስሉ የባንግላዲሽ ወታደሮች ከባድ ስልጠና ሲሰለጥኑ ያሳያል።

ጁንታው (ህወሓት) አንዋጋም ያሉትን የትግራይ ወጣቶችን ረሸናቸው በሚል የተለጠፈው የፌስቡክ ምስል ሐሰተኛ ነው።

ልጥፉ ላይ በአማርኛ ቋንቋ የተጻፈው ጽሁፍ “ጁንታው አንዋጋም ያሉትን ወጣቶችን እረሸናቸው።እግዚኦ ! የትግራይ ወጣቶች አለቁ” ይላል፡፡

ያንዴክስ የምስል ፍለጋ (Yandex image search) ውጤት እንደሚያሳየው ይህ ምስል እ.ኤ.አ ጥቅምት 3 ቀን 2019 ከተለቀቀው የዩትዩብ ቪዲዮ ልባስ (Thumbnail) የተወሰደ ሲሆን ምስሉ በቪዲዮው 01፡13ተኛ ደቂቃ ላይ ይገኛል።

በቪዲዮው ላይ የባንግላዴሽ ወታደራዊ አካዳሚ ለባንግላዴሽ ጦር ሠራዊቶች አካላዊና አዕምሮአዊ ፅናት ለማጎልበት ያሰበ ከባድ ሥልጠና ሲያሰለጥን ያሳያል።

ይህ ምስል በልጥፉ ላይ የህወሓት አማጺያን አድርገውታል የተባለውን ድርጊትን ባይገልጽም አማጺው በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች ንጹሃኖችን መግደሉን የተለያዩ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ጦርነቱ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች በመስፋፋቱ አካባቢዎቹን የተቆጣጠሩት የህወሓት አማጺያን በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት እያደረሱ ነው የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

 በማይካድራም  የአማራ ብሔር ተወላጅ የሆኑ ንፁሃን ዜጎችን ህወሓት እንደገደለ የተባበሩት መንግሥታት እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያካሄዱት ጥናት ገልጿል።

አርትስ ቲቪ ጁንታው (ህወሓት) አንዋጋም ያሉትን የትግራይ ወጣቶችን እረሸናቸው በሚል የተለጠፈው የፌስቡክ ምስል ተመልክቶ ሐሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

.           .            .           .            .

ይህ ልጥፍ በፌስቡክ እና በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የፔሳቼክ የእውነታ መርማሪዎች በተከታታይ የሚያደርጉት የመረጃ ማረጋገጥ እና የተሳሳተ መረጃን የማጋለጥ ተግባር አካል ነው::

እንደ ፔሳቼክ ያሉ ገለልተኛ ሶስተኛ ወገን የእውነት መርማሪ ድርጅቶች ከፌስቡክ እና የማህበራዊ ድረ ገጾች ጋር በመጣመር የሃሰት ዜናን መለየት እንዲያስችልዎ ይሰራሉ:: ይህን የምናደርገውም በየማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የሚመለከቱት ልጥፍ/ መረጃ መነሻቸውን በማያያዝ እና ጠለቅ ያለ ዕይታ እንዲኖርዎ በማድረግ ነው::

በፌስ ቡክ ላይ የሐሰተኛ መረጃ ወይም የተጭበረበረ የመሰልዎ አጋጣሚ አለ?እንግድያውስ በእዚህ መንገድ ጥቆማ መስጠት ይችላሉ::እንዲሁም ይህን ተጨማሪ ኢንፎርሜሽን በመጠቀም አጠራጣሪ መልዕክቶችን ለመለየት የፔሳቼክ መንገዶችን ማየት ይችላሉ::

https://miro.medium.com/max/400/0*w5yMtCGA1dJdWsaN

ይህ የእውነታ ምርመራ በአርትስ ቲቪ የእውነት መርማሪ ረደኤት አበራ ተጽፎ በፔሳቼክ /አዘጋጅ ኤደን ብርሃኔ አርትኦት የቀረበ ነው::

አንቀጹ ለህትመት እንዲበቃ ያረጋገጠው ደግሞ የፔሳቼክ /አዘጋጅ ኤኖክ ናያርኪ ነው::

https://miro.medium.com/max/394/0*W96t_rnxwPEV6GVv

ፔሳቼክ የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የፋይናንስ መረጃ መርማሪ ተቋም ነው :: ካትሪን ጊቼሩ እና ጀስቲን አርንስቴን በተባሉ ሰዎች የተመሰረተ እንዲሁም በአህጉሪቱ ትልቁ የሲቪክ ቴክኖሎጂ እና የጋዜጠኝነት መረጃ ቋት አቅራቢ በኮድ አፍሪካ የተገነባ ነው:: እንደ ጤና : የገጠር ልማት እና የንጹህ ውሃ አቅርቦት በመሳሰሉ መስኮች ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ከመንግስት የሚጠበቁ አቅርቦቶች ላይ የተጨባጩን ዓለም እይታችንን ሊቀርጹ የሚችሉ በይፋ በሚሰራጩ የፋይናንንስ መረጃዎችን ዙርያ ህብረተሰቡ እውነተኛ መረጃን ማገናዘብ እንዲችል ለማገዝ የሚያስችል ድጋፍ ይሰጣል:: ፔሳቼክ ሚድያዎች የሚያቀርቡትን ጥንቅርም ይፈትናል:: የበለጠ መረጃ ለማግኘት pesacheck.org. ይጎብኙ::

https://miro.medium.com/max/60/0*YkqT49Yqdeot06Pp?q=20
https://miro.medium.com/max/70/0*YkqT49Yqdeot06Pp

Follow Us

https://miro.medium.com/max/54/0*mDTpdvUOWw1Vdz82?q=20
https://miro.medium.com/max/61/0*mDTpdvUOWw1Vdz82

Like Us

https://miro.medium.com/max/60/0*3pOdHCEnn3ovvbS_?q=20
https://miro.medium.com/max/72/0*3pOdHCEnn3ovvbS_

Email Us

ፔሳቼክ ኮድ ፎር አፍሪካ ከዶቼቬለ አካዳሚያ ባገኘው ድጋፍ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሚድያዎች እንዲሁም የሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር ኢኖቬት አፍሪካ ፈንድ በሚለው መስመሩ የሚያቀርበው እንቅስቃሴ ነው::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *