loading
ሐሰት: ይህ ምስል MI-35 የተሰኘ የጦር ሄለኮፕተር በአፋር ክልል ሚሌ ተመቶ አያሳይም።

ምስሉ የተወሰደው ዘ ታይምስ ከተባለ በለንደን የሚገኝ የብሪቲሽ ዕለታዊ ብሔራዊ የጋዜጣ ድህረገስፅ ላይ ነው።

ምስሉ የኢራቅ የጦር ሄሊኮፕተር በሰሜን ኢራቅ በሞሱል አቅራቢያ የሚገኙ የአይሲስ ቦታዎችን ሲደበድብ ያሳያል።

ይህ የፌስቡክ ልጥፍ “#ሰበር #ዜና

#ትግራይ #ትስዕር

የትግራይ ሰራዊት አየር ሀይል ምድብ MI-35 የተሰኘ የጦር ሄለኮፕተር በአፋር ክልል ሚሌ መቶ መጣሉን የትግራይ ሰራዊት ሰንተራል ኮማንድ ቃላቀባይ ጌታቸው ረዳ አስታወቀ።” ይላል።

በሰሜን ኢትዮጵያ፤ ትግራይ ክልል የጀመረው ጦርነት ወደ አፋርና አማራ ክልሎች አድማሱን አስፍቶ ቀጥሏል። በአፋር ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የህወሓት ታጣቂዎች የከፈቱትን ተኩስ ተከትሎ የፌደራል መንግስትና የክልሉ መንግስት ከህወሓት ጋር ጦርነት ውስጥ ናቸው። እስካሁን በግጭቱ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ዜጎች ሕይወት አልፏል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቤት ቀዬያቸውን ጥለው ተፈናቅለዋል፤ የዕለት ርዳታ ጠባቂዎች ለመሆንም ተገደዋል።

ልትፉ የህወሓት አማጺ የጦር ሄለኮፕተር በአፋር ክልል ሚሌ መቶ መጣሉን በምስል በማስደገፍ የሚገልፅ ቢሆንም የጎግል የምስል ፍለጋ (Google reverse image search) ውጤት እንደሚያሳየው የልጥፉ ትክክለኛው ምስል ጥቅምት 23 2016 ዓ.ም ዘ ታይምስ ከተባለ በለንደን የሚገኝ የብሪቲሽ ዕለታዊ ብሔራዊ የጋዜጣ ድህረገስፅ ላይ እንደተለቀቀ ያሳያል።

በክልሉ በአዋሳኝ አከባቢ በሚገኙ ጭፍራ፣ በርሃሌ እና መጋሎ ወረዳዎች አሁን ላይ የጦርነት ቀጠና መሆናቸውንም የክልሉ ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡ 

ይሁን እንጂ በአፋር ክልል የጅቡቲ ኮሪደር ዋና መተላለፊያ የሆነችው ሚሌ በአሁኑ ሰዓት ከአማጺው ነፅ መሆኗንና የከተማዋ በተለመደ የለት ተለት እንቅስቃሴዋ ውስጥ እንደምትገኝ  ተናግረዋል።

አርትስ ቲቪ የህወሓት አማጺ የጦር ሄለኮፕተር በአፋር ክልል ሚሌ መቶ መጣሉን ያሳያል በሚል የተለጠፈው የፌስቡክ ልጥፍ ተመልክቶ ሐሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

.           .            .           .            .

ይህ ልጥፍ በፌስቡክ እና በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የፔሳቼክ የእውነታ መርማሪዎች በተከታታይ የሚያደርጉት የመረጃ ማረጋገጥ እና የተሳሳተ መረጃን የማጋለጥ ተግባር አካል ነው::

እንደ ፔሳቼክ ያሉ ገለልተኛ ሶስተኛ ወገን የእውነት መርማሪ ድርጅቶች ከፌስቡክ እና የማህበራዊ ድረ ገጾች ጋር በመጣመር የሃሰት ዜናን መለየት እንዲያስችልዎ ይሰራሉ:: ይህን የምናደርገውም በየማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የሚመለከቱት ልጥፍ/ መረጃ መነሻቸውን በማያያዝ እና ጠለቅ ያለ ዕይታ እንዲኖርዎ በማድረግ ነው::

በፌስ ቡክ ላይ የሐሰተኛ መረጃ ወይም የተጭበረበረ የመሰልዎ አጋጣሚ አለ?እንግድያውስ በእዚህ መንገድ ጥቆማ መስጠት ይችላሉ::እንዲሁም ይህን ተጨማሪ ኢንፎርሜሽን በመጠቀም አጠራጣሪ መልዕክቶችን ለመለየት የፔሳቼክ መንገዶችን ማየት ይችላሉ::

https://miro.medium.com/max/400/0*w5yMtCGA1dJdWsaN

ይህ የእውነታ ምርመራ በአርትስ ቲቪ የእውነት መርማሪ ረደኤት አበራ ተጽፎ በፔሳቼክ /አዘጋጅ ኤደን ብርሃኔ አርትኦት የቀረበ ነው::

አንቀጹ ለህትመት እንዲበቃ ያረጋገጠው ደግሞ የፔሳቼክ /አዘጋጅ ኤኖክ ናያርኪ ነው::

https://miro.medium.com/max/394/0*W96t_rnxwPEV6GVv

ፔሳቼክ የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የፋይናንስ መረጃ መርማሪ ተቋም ነው :: ካትሪን ጊቼሩ እና ጀስቲን አርንስቴን በተባሉ ሰዎች የተመሰረተ እንዲሁም በአህጉሪቱ ትልቁ የሲቪክ ቴክኖሎጂ እና የጋዜጠኝነት መረጃ ቋት አቅራቢ በኮድ አፍሪካ የተገነባ ነው:: እንደ ጤና : የገጠር ልማት እና የንጹህ ውሃ አቅርቦት በመሳሰሉ መስኮች ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ከመንግስት የሚጠበቁ አቅርቦቶች ላይ የተጨባጩን ዓለም እይታችንን ሊቀርጹ የሚችሉ በይፋ በሚሰራጩ የፋይናንንስ መረጃዎችን ዙርያ ህብረተሰቡ እውነተኛ መረጃን ማገናዘብ እንዲችል ለማገዝ የሚያስችል ድጋፍ ይሰጣል:: ፔሳቼክ ሚድያዎች የሚያቀርቡትን ጥንቅርም ይፈትናል:: የበለጠ መረጃ ለማግኘት pesacheck.org. ይጎብኙ::

https://miro.medium.com/max/60/0*YkqT49Yqdeot06Pp?q=20
https://miro.medium.com/max/70/0*YkqT49Yqdeot06Pp

Follow Us

https://miro.medium.com/max/54/0*mDTpdvUOWw1Vdz82?q=20
https://miro.medium.com/max/61/0*mDTpdvUOWw1Vdz82

Like Us

https://miro.medium.com/max/60/0*3pOdHCEnn3ovvbS_?q=20
https://miro.medium.com/max/72/0*3pOdHCEnn3ovvbS_

Email Us

ፔሳቼክ ኮድ ፎር አፍሪካ ከዶቼቬለ አካዳሚያ ባገኘው ድጋፍ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሚድያዎች እንዲሁም የሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር ኢኖቬት አፍሪካ ፈንድ በሚለው መስመሩ የሚያቀርበው እንቅስቃሴ ነው::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *