loading
መከላከያ ሚኒስቴር ከሜቴክ አመራሮች ጋር ደርባችሁ አትፈርጁኝ አለ

መከላከያ ሚኒስቴር ከሜቴክ አመራሮች ጋር ደርባችሁ አትፈርጁኝ አለ

አርትስ 18/03/2011

በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን/ሜቴክ/ ውስጥ በወንጀል የተጠረጠሩ አመራሮች ጋር በተያያዘ ሰራዊቱን የሚፈርጁ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የመከላከያ ሚኒስቴር አሳሰበ።

ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን/ሜይቴክ/ ውስጥ በወንጀል የተጠረጠሩ አመራርሮች ጋር በተያያዘ ሰራዊቱን ጥፋተኛ አድርገው የሚፈርጁ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ  አሳስቧል፡፡

ሰራዊቱ መንግስት እየወሰደ ላለው የለውጥ እርምጃ የበኩሉን እንደሚወጣ እና የሰራዊቱን አቅም ግንባታ መሰረት ያደረገ ሪፎርም በሰራዊቱ ላይ መደረጉም ተገልጿል።

ተጠርጣሪዎችን የማጋለጥና በቁጥጥር ስር ማዋል ስራ የሚኒስቴሩ አንዱ የሪፎርሙ አካል ሆኖ እየተሰራበት መሆኑም ነው የተገለጸዉ።

ሰሞኑን በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን(ሜቴክ) እንዲሁም በሌሎች ተቋማት ውስጥ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋልም ሚኒስቴሩ አብሮ እየሰራ መሆኑን በመከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ኢንዱክትሪኖሽንና ህዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል መሀመድ ተሰማ ገልጸዋል።

በህዝባዊ ወገንተኝነት ህዝብ በማገልገል ላይ የሚገኘው ሰራዊቱ ለእንዲህ አይነት የወንጀል ተግባር ራሱን መስዋት እስከማድረግ የሚታገል መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ከላይ ከጠተቀሱት ተጠርጣሪዎች ጋር የመፈረጁን ተግባርም እንደሚያወግዝና ግለሰቦቹን ተጠያቂ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *