loading
ሚኒስቴሩ አንድ እሽግ ለአንድ ሴት በሚል መርህ አቅም ለሌላቸው ሴቶች የንፅህና መጠበቂያዎችን ሊሰበስብ ነው

ሚኒስቴሩ አንድ እሽግ ለአንድ ሴት በሚል መርህ አቅም ለሌላቸው ሴቶች የንፅህና መጠበቂያዎችን ሊሰበስብ ነው።

 

የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚኒስቴር ለ16ኛ ጊዜ በሚካሄደውና በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሚዘጋጀው የ 5ኪ.ሜ. የሴቶች ሩጫ አቅም ለሌላቸው ሴቶች የንጽህና መጠበቂያዎችን ለመሰብሰብ ማቀዱን ተናግሯል።

‹‹ እኔም የመሪነት ድርሻዬን እወጣለሁ›› በሚል መርህ በሚካሄደው በዚሁ ሩጫ ላይ የሚካሄደው የ አንድ እሽግ ለአንድ ሴት ዘመቻ አቅም ለሌላቸው ሴቶች የንጽህና መጠበቂያዎችን ለማሰባሰብና ለማከፋፈል ያግዛል ተብሏል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ማርኬቲንግ ሃላፊ ወ/ሪት ህሊና ንጉሴ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት ሩጫው መጋቢት 1 ቀን 2011 አ.ም የሚካሄድ ሲሆን ከዚሁ ጎን ለጎን የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ከታላቁ ሩጫ እና ከቀይ መስቀል ጋር በመተባበር በወሊድ ምክንያት የሚሞቱ እናቶችን በማሰብም የደም ልገሳ ፕሮግራም ያካሄዳል፡፡

በሩጫው ከ13 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይገኛሉ ያሉት ሃላፊዋ ሩጫው ላይ የሚገኙ ተሳታፊዎች  ከ1 እሽግ ጀምሮ የንፅህና መጠበቂያ ይዞ በመምጣት እና በመለገስ አቅም የሌላቸውን እህቶች እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ታላቁ ሩጫ ይህን የሴቶች ሩጫ ሲያዘጋጅ የዘንድሮው ለ16ኛ ጊዜ ሲሆን አትሌት መሰረት ደፋርም የዚሁ ሩጫ አምባሳደር መሆኗ ይታወቃል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *