loading
ማላዊ በቮሮናቫይረስ ሳቢያ ሁለት የካቢኔ ሚኒስትሮቿን ማጣቷ በሀገሪቱ ትልቅ ሀዘን ፈጥሯል፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 05፣ 2013 ማላዊ በቮሮናቫይረስ ሳቢያ ሁለት የካቢኔ ሚኒስትሮቿን ማጣቷ በሀገሪቱ ትልቅ ሀዘን ፈጥሯል፡፡ የማላዊ ፕሬዳንት ላዛረስ ቺኩየራ የሚንስትሮቹን ሞት አስመልክተው ባደረጉት ንግግር የማይሰላ ኪሳራ ደርሶብናል ካሉ በኋላ በሀገሪቱ የሶስት ቀን ሀዘን መታወጁን ይፋ አድርገዋል በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ ህይዎታቸው ያለፈው የትራንስፖርት ሚስትሩ ሲዲክ ሚያ እና የአካባቢ አስተዳደር ሚንስትሩ ሊንግሰን ብሬካኒያማ ናቸው፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ሚኒስትሮቹ ቀደም ብሎ በነበረው ጊዜ ስብሰባዎችን የተካፈሉ በመሆናቸው ሌሎች ፖለቲከኞች በበሽታው እንዳይያዙ ስጋትን ፈጥሯል ነው የተባለው፡፡ ይሁን እንጂ ሚኒስትሮቹ በስብሰባው ወቅት ይሁን በገና በዓል አከባበር ሰሞን በየትኛው ወቅት እንደተያዙ ፍንጭ የሰጠ አካል የለም፡፡
በሁኔታው የተደናገጠው የማላዊ መንግስት በመላ ሀገሪቱ አስቸኳይ የአደጋ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ ደንግጓል፡፡

ማላዊ ከ9 ሺህ በላይ ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 30 በመቶ የሚሆኑት በባለፉት 2 ሳምንታት ብቻ መሆኑ የሥርጭቱ መጠን በፍጥነት እየጨመረ ለመሆኑ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡ ፕሬዚዳንት ቺኩየራ ህዝባቸው ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጠውን የኮቪድ 19 መመሪያዎች ጠንቅቆ እንዲያውቅና ተግባራዊ እንዲያደርግ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *