loading
ማንችስተር ሲቲ የካራባዎ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ ።

ማንችስተር ሲቲ የካራባዎ ዋንጫ አሸናፊ ሆነሆነ ።

የ2018/19 የእንግሊዝ ፉትቦል ሊግ ዋንጫ (ካራባዎ ዋንጫ) የፍፃሜ ግጥሚያ ዌምብሌይ ስታዲየም በቼልሲ እና ማንችስተር ሲቲ መካከል ተካሂዶ በሰማያዊዎቹ ድል አድራጊነት ተጠናቅቋል፡፡
በምሽቱ የዋንጫ ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለግብ በአቻ ውጤት አጠናቀቁ፡፡ በተጨማሪው የ30 ደቂቃ ጨዋታም ግብ ባለመቆጠሩ በተሰጠው የመለያ ፍፁም ቅጣት ምት በውሃ ሰማያዊዎቹ 4 ለ 3 አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡
የመለያ ፍፁም ቅጣት ምቱን በቼልሲ በኩል የመቱት፤ አዚፕሊኮይታ፣ ኤመርሰን እና ሀዛርድ ቢያስቆጥሩም ሊዊዝ እና ጆርጂኒዮ ግን አምክነዋል፡፡
ሲቲን ሻምፒዮን ያደረጉ ጎሎች ጉንዶሃን፣ አጉዌሮ፣ በርናርዶ ሲልቫና ስተርሊንግ ከመረብ ሲያገናኙ፤ የሊሮይ ሳኔ ምት በኬፓ አሪዛባላጋ ጎል ከመሆን ብትድንም ማንችስተር ሲቲን ግን የዋንጫው ባለቤት ከመሆን አላገደውም፡፡
የቼልሲው ግብ ጠባቂ በኬፓ አሪዛባላጋ ጭማሪው ደቂቃ እየተጠናቀቀ ባለበት ጊዜ በካባዬሮ እንዲቀየር በሳሪ ትዕዛዝ ተላልፎለት የነበረ ቢሆንም የአሰልጣኙን ትዕዛዝ ባለመቀበል ሳይቀየር ቀርቷል፡፡
ማንችስተር ሲቲ የካራባዎን ዋንጫ በተከታታይ ሁለት ዓመት ያሳካ ሲሆን ፔፕ ጓርዲዮላ ከሚፎካከርባቸው አራት ውድድሮች ውስጥ የዓመቱን የመጀመሪያ ዋንጫ አሳክቷል፡፡
የጣሊያናዊው አሰልጣኝ ማውሪዚዮ ሳሪ የዋንጫ ያለማንሳት ታሪክም እንደቀጠለ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *