loading
ማንችስተር ዩናይትድንና ሶልሻዬርን የሚያቆማቸው ጠፍቷል

ማንችስተር ዩናይትድንና ሶልሻዬርን የሚያቆማቸው ጠፍቷል

ቀያይ ሰይጣኖቹ ሞሪንሆን አሰናብተው የቀድሞ ተጫዋቻቸውን ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር በአሰልጣኝነት ከቀጠሩ በኋላ በተከታታይ በድል መንገድ ላይ ቢገኙም ጉዟቸው በቶተንሃም ትናንት ሊገታ እንደሚችል ተገልፆ ነበር፡፡

ይሁን እንጅ በግዙፉ ዊምብሌ ስታዲዬም ያደረገውን የፕሪምየር ሊግ 22ኛ መርሀግብር ግጥሚያ ተፈትኖም ቢሆን በጠባብ የግብ ልዩነት አሸንፎ ወጥቷል፡፡

ጨዋታውን ማንችስተር 1 ለ 0 ሲረታ የድል ጎሏን ወጣቱ ማርኮስ ራሽፎርድ ከፖል ፖግባ የተሻገረለትን ኳስ በጥሩ አጨራረስ የመጀመሪያው አጋማሽ ከመጠናቀቁ በፊት በማስቆጠር ቡድኑን አሸናፊ አድርጎታል፡፡

በቶተንሃም በኩል ወደ አስራ አንድ የሚጠጉ ሙከራዎችን ቢያደርጉም አንዱንም ቢሆን ወደ ግብነት መቀየር አልቻሉም፤ ለጎሎቹ አለመቆጠር ደግሞ የግብ ጠባቂው ዴቪድ ዴሂያ ምርጥ ብቃት ላይ መገኘት ሲሆን ቡድኑን ከሽንፈትና ነጥብ ከመጣል መታደግ ችሏል፡፡ ዩናይትዶችም ቢሆን በተለይ በፖግባ አማካኝነት የግብ ሙካራዎች ሲደረጉ ነበር፡፡

ይህን ተከትሎ ዩናይትድ ከአርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ መጠን በዕኩል 41 ነጥብ ማስተካከል ችሏል፡፡

በትናንትናው ዕለት በተደረገ ሌላ ጨዋታ ኢቨርተን በሜዳው በርንማውዝን አስተናግዲ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል ፡፡

ዛሬ ምሽት 5፡00 ማንችስተር ሲቲ ኢቲሃድ ላይ ወልቭስን ያስተናግዳል፡፡

ሊጉን ሊቨርፑል በ57 ነጥብ ይመራል፤ ማ.ሲቲ ደግሞ በ50 ይከተላል፤ ቶተንሃም በ48 እንዲሁም ቼልሲ በ47 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፤ አርሰናልና ማንችስተር ዩናይትድ በዕኩል 41 ነጥቦች በግብ ክፍያ ተበላልጠው አምስተኛና ስድስተኛ ደረጃን ተቆናጠዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *