ማይክፔንስ ትራምፕ ከኪም ጋር ዳግም ሲገናኙ የቀድሞውን ስህተት አይደግሙትም አሉ
አርትስ 06/03/2011
የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ ትራምፕ በፈረንጆቹ 2019 ከሰሜን ኮሪያው አቻቸው ኪም ጆንግ ኡን ጋር የመገናኘት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
ይሁንና ከአሁን በፊት የተፈጸሙ ስህተቶች እንዳይደገሙ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረጋል ብለዋል ፔንስ፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው የሁለቱ ሀገራ መሪዎች ባለፈው ሰኔ ወር የተካሄደውን የሲንጋፖሩን ስብሰባ ውጤት ለመገምገምና የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ቅነሳ ላይ ለመወያያት ሁለተኛውን ቀጠሮ ይዘዋል፡
ሁለቱ መሪዎች በአዲሱ የፈረንጆቹ ዓመት መጀመሪያ ላይ ይገናኛሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን ያሉት ፔንስ መቸ እና የት የሚለው ግን በሂደት የሚታወቅ ይሆናል ብለዋል፡፡
ፔንስ ከአሁን ቀደም የተሰሩ ስህተቶች ያሉት ላለፉት ዓመታት በቀድሞዎቹ መሪዎች ብዙ ቃልኪዳኖች ተገብተው፣ ማዕቀቦች እንዲነሱ ተደርገው እስካሁን ድረስ የተገቡ ውሎች አለመፈፀማቸው እንደሆነ አብራርተዋል፡