loading
ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው መንግስት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ፍርድ ቤቱን ጠየቁ

አርትስ 06/03/2011

የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው ትናንት ችሎት ፊትቀርበዋል።

በዕለቱ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውና ጋዜጠኛ ፍጹምየሽጥላን ጨምሮ 8 ተጠርጣሪዎች ቀርበዋል። ከዚህ ውስጥ ሁለቱ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲሆን ስድስቱ ደግሞ በሙስናወንጀል ተጠርጥረው የቀረቡ ናቸው።

በሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው ላይ ከቀረበው የአቤቱታ መዝገብ ዋና ዋና ጭብጦች፤ ሜቴክ ባሉት 10 ኢንዱስትሪዎች ድጋፍእንዲሰሩ የተያዙ ፕሮጀክቶችን ማጓተት፤ ከያዩ ማደበሪያ፣ ስኳር ፋብሪካዎች እና የታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር የተገናኙ ጉዳዮች፤የህዝብና የመንግስት ንብረት እንዲባክን ማድረግ የሚሉትና ሌሎች ክሶች ቀርበውባቸዋል፡፡

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ፍጹም የሽጥላም ፍርድ ቤት የቀረበችው፤ ከሜቴክ ጋር በተያያዘ በሙስና ወንጀልተጠርጥራ ነው።

ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው በጡረታ የሚያገኙት ወርሃዊ ገቢያቸው 4 ሺህ ብር በመሆኑ እንዲሁም አቅም የሌላቸውዘመድም ከማስቸግር በማለት መንግስት ተከላካይ ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ችሎቱን ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮቴሌኮም ሰራተኛ ሆነው የግዢ ስርዓቱን በጣሰ መልኩ ሜቴክ ጨረታ እንዲያሸንፍ በማድረግ ወንጀል ተጠርጥረውፍርድ ቤት የቀረቡት ወንድማቸው አቶ ኢሳያስ ዳኘው ደግሞ ወራሀዊ ደሞዛቸው 8 ሺህ ብር በመሆኑ በተመሳሳይ መንግስትጠበቃ ማቆም አልችልም ብለዋል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት፤ የተጠርጣሪዎቹን ጥያቄ በመቀበል ግለሰቦቹ ከተመደበላቸው ተከላካይጠበቃ ጋር ፍርድ ቤቱ ለዛሬ ከሰዓት በኋላ 8 ሰዓት እንዲቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ኤፍ ቢ ሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *