loading
ምርጫ ከመደረጉ በፊት ያሉት አራት ቀናት የጥሞና ወቅት ናቸዉ ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9፣ 2013   ምርጫ ከመደረጉ በፊት ያሉት አራት ቀናት የጥሞና ወቅት በመሆናቸዉ የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ  እንደማይደረግባቸዉ ተገለፀ የጥሞና ወቅት በቅድመ የምርጫ ዑደት ውስጥ የሚገኝ ጊዜ ሲሆን በኢትዮጵያ የምርጫ ዑደት መመሪያ መሠረት ምርጫ ከመደረጉ በፊት ያሉትን አራት ቀናት ያካትታል የሚያትት ነው፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎች እና ደጋፊዎቻቸው ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሚየካሂዱት የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ ድምጽ መስጠት ከመጀመሩ ከአራት ቀን በፊት መጠናቀቅ እንዳለበት ቦርዱ ገልጿል፡፡ በነዚህም አራት ቀናት ማንኛውም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ በበይነ መረብ ፣
በማህበራዊ ሚዲያ በግንባር ቤት ለቤት በአደባባይ በአዳራሽ ስብሰባ ምንም አይነት ቅስቀሳ ማከናወን በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን እና ፓርቲዎችም መመሪያዎቹን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸው ተገልጿል፡፡

የመገናኛ ብዙሀን ተቋማትም በዚህ ወቅት ማንኛውንም ምርጫ ተኮር እንቅስቃሴዎችን ማሰራጨት በተጨማሪም የፓለቲካ ፓርቲ እጩዎችን አግኝተው ቃለ መጠይቆችን መስራት በምርጫ መመሪያው የተከለከለ መሆኑን ቦርዱ በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ አስታውቋል፡፡ የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሚወጡ መረጃዎችን ለህዝቡ በማስተላፍ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን  ከዚህ ውጪ በመመሪያዎች ላይ ያልተደነገጉ ተግባራትነ ቢፈፅሙ በህግ ተጠያቂነት እንደሚኖርባቸው ተጠቁሟል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *