loading
ምንጋግዋ ፑቲንን ሀገሬን ለማልማት ቀኝ እጅዎን ያውሱኝ እያሏቸው ነው

ምንጋግዋ ፑቲንን ሀገሬን ለማልማት ቀኝ እጅዎን ያውሱኝ እያሏቸው ነው፡፡

የዚምባብዌው ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የፑቲንን ድጋፍ ፍለጋ ባለስልጣኖቻቸውን አስከትለው ሞስኮ ገብተዋል፡፡

በሀገር ቤት በዋጋ ንረት ሳቢያ  የተቃውሞ ሰልፍ ረፍት የነሳቸው ምናጋግዋ ክሬምሊን ከገቡ በኋላ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ሀገሬ ከኢኮኖሚ ችግር ትላቀቅ ዘንድ እንደታላቅ ወንድም አቅፈው ደግፈው እንዲያግዙኝ አፈልጋለሁ ብለዋቸዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ኤመርሰን ምናንጋግዋ ሩሲያን ጨምሮ አምስት ሀገራትን ለመጎብኘት እቅድ ይዘው ነው ከሀራሬ የወጡት፡፡

የሩሲያው ጉብኝት ዋነኛ ዓላማ በዚምባቡየ የተከሰተውን የኢኮኖሚ አለመገረጋጋት  ፈር ለማስያዝ የቭላድሚር ፑቲን አስተዳደር ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ለማግባባት ነው ተብሏል፡፡

ምናንጋዋ ከፑቲን ጋር ሲወያዩ የሀራሬ እና የሞስኮ ግንኙነት በፖለቲካው መስክ የተዋጣለት ስለመሆኑ አልጠራጠርም የኢኮኖሚው ዘርፍ ግን ብዙ ስራ ይጠይቃል፤ ለዚህም የታላቅ መድሜ ፑቲን ድጋፍ እንደማይለየኝ እተማመናለሁ ብለዋል፡፡

ፑቲን በበኩላቸው ለጀመሪያ ጊዜ ክሬምሊን የተገኙትን ምናንጋግዋን እንኳን ደህና መጡ ካሉ በኋለ መንግስታቸው ለዚምባብዌ ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ለማድረግ  ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠውላቸዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ውይይት በሀገራቱ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር  ለማጠናከር ጥሩ  መግባባት ላይ መድረሳቸውን ከክሬምሊን የወጣ መረጃ ያመላክታል፡፡

ፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ ባለፈው ዓመት ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ሀገሪቱን የመሩትን የቀድሞ አለቃቸውን ሮበርት ሙጋቤን አስወግደው ስልጣን ከያዙ ጀምሮ ተፈላጊውን ለውጥ ማምጣት ተስኗቸዋል እየተባሉ ይተቻሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *