loading
ምክትል ከንቲባው ለአድዋ ተጓዦች ሽኝት አደረጉ::

ምክትል ከንቲባው ለአድዋ ተጓዦች ሽኝት አደረጉ::

የአድዋ ድልን ለመዘከር ለስድስተኛ ጊዜ የሚደረገው የእግር ጉዞ ተጓዦችን ለመሸኘት በአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር ቅጥር ግቢ ውስጥ የሽኝት ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡

በሽኝቱ ላይ የከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጅነር) ፣ የካቢኔ አባላት፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ፣ የሃይማኖት አባቶች እና አባገዳዎች እንዲሁም  የከተማው ነዋሪዎች  ተገኝተዋል፡፡

የጉዞ አድዋ ዋና አስተባባሪ ያሬድ ሹመቴ ለአርትስ ቴሌቭዥን እንደተናገረው በዚህ መልኩ የሽኝት ስነ ስርዓት ሲደረግላቸው የመጀመሪያው ነው፡፡

አስተባባሪው እንዳለው በዚህ አመት ከአዲስ አበባ የተወጣጡ 44   እዲሁም 4 የሀረር ተጓዦች ተሳታፊ ሁነዋል፡፡

ይህ የእግር ጉዞ ለ61 ቀናት የሚደረግ ሲሆን ከ1ሺህ በላይ ኪሎ ሜትሮችን ይሸፍናል፡፡

የእግር ጉዞው  በዓሉን በመዘከር ላለፉት 5 አመታት ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *