loading
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2013 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ፡፡ አቶ ደመቀ ከፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ ጋር ፕሪቶሪያ ተገናኝተው ባደረጉት ውይይት በሁለቱ አገሮች የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት ማዳረጋቸው ተመልክቷል፡፡ ምክትል ጠቅላይ መኒስትሩ በውይይታቸው ወቅት በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ጉዳዮች በተመለከተ ለፕሬዚዳንት ራማፎዛ ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡

በትግራይ ክልል ህግ የማስከበር እርምጃን ተከትሎ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ በስፋት ተደራሽ እየተደረገ መሆኑን አቶ ደመቀ ገልፀዋል። ከሰብአዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጉዳዮችን በመመርመር ተጠያቂ የሆኑትን ለሕግ ለማቅረብ መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት እና የተሰሩትን ስራዎችም በዝርዝር ገልፀዋል።
የህዳሴ ግድቡን አስመልክቶ በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሶስትዮሽ ድርድር እንዲቀጥል ኢትዮጵያ ያላትን ፅኑ አቋም አስረድተዋል።

ስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ በተሳካ መልኩ ለማካሄድ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑንም መግለፀቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ አቶ ደመቀ ፕሬዚዳንት ራማፎዛ ለአፍሪካውያን ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ መፈለግ መርህ በማራመድ
ያሳዩትን የመሪነት ሚና አድንቀዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *