ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሴራሊዮን ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር ተወያዩ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሴራሊዮን ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር ተወያዩ፡፡
ሀበሻ ለፍቅር የሚል ማህበር ያቋቋሙት የኮሚኒቲ አባላቱ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በኢትዮጵያ ስላለው የለውጥ እንቅስቃሴ እና በዳያስፖራው ተሳትፎ፣ እንዲሁም ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
አሁን በኢትዮጵያ ባለው ለውጥ ደስተኞች መሆናቸውን የገለጹት የኮሚኒቲ አባላቱ ለውጡ በመካከለኛውና በታችኛው እርከንም ሊተገበር ይገባል ብለዋል፡፡
በሀገሪቱ የሚስተዋለውን ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመከላከል በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ሊተገበር እንደሚገባም በውይይታቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡
“ለያዝናቸው የለውጥ መንገዶች ትልቁ ደጋፊያችንና አጋራችን በውጪ የሚኖረው ማህበረሰብ ነው” ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የለውጡ ጉዞ እንዲሳካ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ዘገባው የኢቢሲ ነው፡፡