ሩስያ በሺዎች ሚቆጠሩ የሰሜን ኮሪያ ዜጎች በሀገሯ ገብተዉ እንዲቀጠሩ ፈቀደች፡፡
ሞስኮ ታይምስ ከመቀመጫዉ ከሞስኮ እንደዘገበዉ በሩሰያ ከ10 ሺ በላይ ሰሜን ኮርያዉያን የስራ ፍቃደ ማግኘታቸዉን አረጋግጠዋል፡፡
ሩስያ የወሰደችዉ እርምጃ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፒዮንግያንግ ዜጎች ላይ ከሀገር ወጥተዉ እንዳይሰሩ የተጣለባቸዉን ማእቀብ የጣሰ ነዉ ተብሏል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ጉዳዩን እያጣራሁ ነዉ ብሏል፡፡
ሩስያ ግን ስለጉዳዩ ለማንም ምላሽ አልሰጠችም፡፡
እስካሁን ሩስያ ዉስጥ የሚኖሩ ሰሜን ኮርያዉያን ወደሀገራቸዉ በየአመቱ እስከ 300 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ይልካሉ፡፡