loading
ሪያድ ወደ ውጭ የምትልከውን የነዳጅ መጠን ልትቀንስ ነው፡፡

ሪያድ ወደ ውጭ የምትልከውን የነዳጅ መጠን ልትቀንስ ነው፡፡

ሳውዲ አረቢያ ከመጭው መጋቢት ወር ጀምሮ በቀን ወደ ውጭ ትልከው የነበረውን 8.2 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ወደ 6.9 ሚሊዮን በርሜል ዝቅ ልታደርግ መሆኑን ተናግራለች፡፡

የሳውዲ የኢነርጂ ሚኒስትር ካሊድ አል ፋሊህ ለፋይናንሺያል ታይምስ እንደተናገሩት ሪያድ ወደ ውጭ የምትልከውን ነዳጅ ብቻ ሳይሆን የምርት መጠኗንም የመቀነስ ሃሳብ አላት፡፡

በዓለም አቀፉ የነዳጂ ላኪ ሀገራት ኦፔክ ስምምነት መሰረት ሳውዲ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2019 ጀምሮ 10.311 በርሜል ነዳጅ ለማምረት እቅድ ነበራት፡፡

አሁን የተሰማው መግለጫ እንደሚያሳየው ግን ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ 9.8 ሚሊዮን በርሜል ብቻ ታመርታለች፡፡

ሚኒስትሩ እንዳሉት የመንግስት ንብረት የሆነው ሳውዲ አማሮ የነዳጂ ድርጂት ዓለም አቀፍ የነዳጅ ፍለጋ ስራ ላይ ለመሰማራት እና ገበያውን የማስፋፋት እቅድ አለው፡፡

ይህን የምናደርገው የገሪቱን ሀብት አሟጠን ከመጠቀም ይልቅ ሌላ አማራጭ ለመጠቀም ነው ብለዋል ፋሊህ፡፡

ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች የሚሰነዘረውን  ትችት አስመልክተው ሲናገሩም ሁሉም በየፊናው የመሰለውን ቢናገርም እኛ ትክክለኛው መንገድ ላይ መሆናችንን ጠንቅቀን እናውቃለን ነው ያሉት ሚኒስትሩ፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *