loading
ሰማያዊ ፓርቲ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባትና ኢዴፓ ተዋሀዱ

ሰማያዊ ፓርቲ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባትና ኢዴፓ ተዋሀዱ

አርትስ 21/04/2011

 የተመሠረተበትን ሰባተኛ ዓመት ትናንት ያከበረው  ሰማያዊ ፓርቲ፣ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ጋር ውህደት ለመፈጸም የሚያስችሉ ሥራዎችን  አስቀድሞ ማጠናቀቁን፣ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ለአርትስ ገልፀዋል፡፡

ፓርቲዎቹ እስከ መጋቢት መጨረሻ አዲስ ስም በጋራ ይፋ እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል፡፡

የፓርቲው ሰባተኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ዛሬ ሲከበር የፓርቲዎቹን ውህደት በተመለከተ  በየደረጃው ውይይት የተደረገበት በመሆኑ በጉባዔው መጨረሻ ፀድቋል፡፡

ረቡዕ ታኅሳስ 17 ቀን 2011 ዓ.ም. በወቅታዊ ጉዳዮችና እየተከናወነ ስላለው የውህደት እንቅስቃሴ ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታና የሕዝባችንን የዘመናት ጥያቄ የሚመልስ እንደሚሆን እናምናለን›› በሚል ርዕስ በፓርቲው አመራሮች በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፣ ፓርቲዎች በጋራ በመሥራት ለፖለቲካዊ ችግሮችና ለሕዝቡ ጥያቄዎች የማያዳግም ምላሽ መስጠት እንደሚጠበቅባቸው በአፅንኦት ማስታወቃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

በጠቅላላ ጉባዔው ላይ ከመላው የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ የጉባዔው አባላት የተሳተፉ ሲሆን  ፓርቲው በሰባት ዓመታት የትግል ወቅት ያበረከተው ጉልህ አስተዋጽኦ ዘክሯል፡፡

ባለፉት ዓመታት ፓርቲው ያከናውነው ጥረት ፍሬ አፍርቶ እነሆ በአሁኑ ወቅት ከአርበኞች ግንቦት ሰባት፣ ከኢዴፓና ከሌሎች ጋር ውህደት በመፈጸም ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቆመ በጠንካራ መሠረት ላይ የተዋቀረ ፓርቲ በጋራ ለመመሥረት በቅተናል  በማለት ፓርቲው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጋራ ለመሥራት ሲያደርገው የነበረው ጥረት ወደ መሳካት ደረጃ መድረሱን አቶ የሺዋስ ገልፀውልናል፡፡

አዲሱ ፓርቲም ለአገር ሰላም እንዲሁም ቀጣዩ ምርጫ ውጤታማ እንዲሆን የድርሻውን ይወጣል ብለዋል አቶ የሺዋስ፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *