ሰሜን ኮሪያ በድብቅ ሚሳኤል ማበልፀጓን አላቆመችም ተባለ
አርትስ 04/03/2011
መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው ቲንክ ታንክ ቡድን አገኘሁት ባለው መረጃ ፒዮንያንግ በመላ ሀገሪቱ ከደርዘን በላይ የባለስቲክ ሚሳኤል ጣቢያወችን በድብቅ እያስፋፋች ነው ብሏል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው 20 ከሚሆኑ ድብቅ የሚሳኤል ጣቢያዎች መካከል 13ቱ በተለያዩ የሀገሪቱ ተራራማ አካባቢወች ተራርቀው መገንባታቸውን የሳተላይት ምስሎች ያሳያሉ፡፡
ይህ ሁኔታ ደግሞ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፒዮንግያንግ ያሳየቸው መሻሻል ሊታመን የማይችል ነው ያሉለትን ጉዳይ ከንቱ ያስቀራል ተብሏል፡፡
ትራምፕና ኪም በቅርቡ ሊያካሂዱት የነበረው ስብሰባ ሲራዘም ምክንያቱ ሰሜን ኮሪያ ዝግጁ ስላልሆነች ነው የሚለው መግለጫ አሁን ለሚባለው ነገር ፍንጭ ነው የሚሉም አልጠፉም፡፡
ሰሜን ኮሪያ ባለፈው ወር በአሜሪካ ማእቀብ ያላትን ቅሬታ ስትገልፅ ዋሽንግተን ሀሳቧን የማትቀይር ከሆነ ወደ ቀደመው ፖሊሲያችን እንመለሳለን ማለቷ የሚታወስ ነው፡፡