loading
ሰሞኑን ፈረንሳይ ውስጥ በተቀሰቀሰ የእሳት አደጋ ሁለት ህፀናትን ያዳኑ ሰዎች ከከንቲባቸው ጀግኖች የሚል ውዳሴ ተችሯቸዋል::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ16፣ 2012ሰሞኑን ፈረንሳይ ውስጥ በተቀሰቀሰ የእሳት አደጋ ሁለት ህፀናትን ያዳኑ ሰዎች ከከንቲባቸው ጀግኖች የሚል ውዳሴ ተችሯቸዋል::የሶስት እና የአስር ዓመት ያላቸው እመነዚህ ህፃና የሚኖሩበት አፓርታማ በእሳት ሲጋይ ከሶስተኛ ፎቅ መውጫ አጥተው ህዝቡ ከታች ከቦ ይመለከት ነበር፡፡ሰዎቹም ህፀናቱ በመስኮት እንዲዘሉ እና ጉዳት ሳይደርስደባቸው እንደሚቀበሏቸው በማበረታታት የህፀናቱን ህይዎት መታግ ችለዋል ነው የተባለው፡፡ህፀናቱም እሳቱ እየበረታ ሲመጣ ከንጻው ስር የተሰባሰቡትን ሰዎች በማመን ከሶስተኛ ፎቅ ሳያመመነቱ ሲዘሉ ታይተዋል፡፡

ሰዎቹም ተረባርበው ህፃናቱን ከእሳቱም ወድቀው ከመሰባበርም ሲያድኗው እነሱ ግን እጆቻው ላይ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል እንደተወሰዱ የመገናኛ ብዙሃን ተቀባብለው ዘግበውታል፡፡በዚህ ተግባራቸውም ህፀናቱን ያዳኑትን ግለሰቦች የግሬኖብል ከተማ ከንቲባ ኤሪክ ፒዮል ጀግኖቻችን ነናቸው ሲሉ አሞካሽተቸዋል፡፡በእሳት አደጋው ሳቢያ በአፓርትመንቱ ነወዋሪዎች የሆኑ 17 ሰዎች መቁሰላቸውን የከተማዋ የእሳት አደጋ መከላከል ክፍል ገልጿል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *