loading
ሱዳን የሴት ልጅ ግርዛትን በወንጀል ህጓ አንዲያስቀጣ ደነገገች::

ሱዳን የሴት ልጅ ግርዛትን በወንጀል ህጓ አንዲያስቀጣ ደነገገች::

የሱዳን መንግስት የሴት ልጅ ግርዛት ሲፈፅሙ የተገኙ ግለሰቦች በሶስት ዓመት እስራት እንዲቀጡ የሚደነግግ አዲስ ህግ አፅድቋል፡፡አዲሱ የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ህን ሲያፀድቅ በቤት ውስጥም ይሁን በህክምና ተቋማት ይህን ተግባር ሲያከናውኑ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ በሶስት ዓመት እስራ እና በገንዘብ ይቀጣል ብሏል፡፡አልጀዚራ የተባበሩት መንግስታትን መረጃ ጠቅሶ እንደዘገበው በሱዳን ከአስሩ ሴቶች ዘጠኙ ግርዛት ይፈፀምባቸዋል፡፡

በሀገሪቱ የሴት ልጆች ግርዛት እንዲቆምና ይህን የሚያደርጉ ሰዎች በህግ እንዲጠይቁ ሲታገሉ የነበሩ የሴቶች መብት ተከራካሪዎች የህጉን መፅደቅ ለሱዳን ልጃገረዶችና ህፃናት አዲስ የተስፋ ዘመን ብለውታል፡፡ይሁን እንጂ የሰዎችን አስተሳብ በቀላሉ መቀየር ስለሚያስቸግር ህጉን ከማስከበር ጎን ለጎን በሰፊው ሊሰራበት ይገባል ተብሏል፡፡እንዲህ አይነቱ በሴት ልጆች ላይ የጤና ጉዳት የሚያደርሰው ተግባር 27 በሚሆኑ የአፍሪካ ሀገራት፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በከፊል የእስያ ሀገራት አሁንም የማህረሰብ ችግር ሆኖ እንደቀጠለ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *