ሱዳን ጋዜጠኞችን ከእስር ለቀቀች፡፡
ሱዳን ጋዜጠኞችን ከእስር ለቀቀች፡፡
የፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር መንግስት በሀገሪቱ የተቀሰቀሰውን አመፅ ለማብደረድ ሲል በገባው ቃል መሰረት ነው አስራ አንድ ጋዜጠኞችን የፈታው፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ጋዜጠኞቹ በሱዳን የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ አመፅ በሚዘግቡበት ወቅት ነው በፀጥታ ሀይሎች ተይዘው የታሰሩት፡፡
ለአልበሽር አስተዳደር ታማኝ የሆነው የሱዳን መገናኛ ብዙሀን ማእከል ከተፈቱት ጋዜጠኞጭ መካከል የሱዳን ኮሞኒስት ፓርቲ ንብረት የሆነው አል ሚዳን እለታዊ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ይገኝበታል ሲል አስነብቧል፡፡
የአልበሽርን እርምጃ እንደ አንድ ጥሩ ጅምር አድርገው የተመለከቱ ወገኖች ለሙያው ክብር እንደመስጠት ይቆጠራል ሲሉ የጋዜጠኞቹን መፈታት አድንቀዋል፡፡
አንዳንዶቹ አስተያየት ሰጭዎች ደግሞ እርምጃውን አልበሽር አመፁ አልበርድ ሲል እጅ መስጠት ጀምሩ በማለት ገልፀውታል፡፡
መንገሻ ዓለሙ