loading
ሳማንታ ፓወር በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ገንቢ ሀሳቦችን አንስተዋል::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 29፣ 2013 የዩ ኤስ ኤድ ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ገንቢ ሀሳቦች ማንሳታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ:: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምበሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ሳማንታ ፓወር በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ገንቢ ሀሳቦች ማንሳታቸውን ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል መንግስት እየሰራቸው ያሉ የሰብዓዊ እርዳታ ስራዎችን ከሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ጋር በነበራቸው ውይይት በቂ ማብራሪያ መሰጠቱንም ጠቆመዋል፡፡

መንግስት በትግራይ ክልል የወሰደው የተናጥል የተኩስ አቁም ስምምት አስፈላጊና ወሳኝ መሆኑን ከሳማንታ ፓወር ጋር መነጋገራቸውንም ነው አምባሳደር ዲና የተናገሩት፡፡ የዩ ኤስ ኤድ ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በምዕራብ ኢትዮጵያ በሱዳን በኩል ለአሸባሪው ህዋሃት መንገድ ለማስከፈት ዓላማ ነበራቸው በሚል ለተናፈሰው ሀሳብ በጉብኝታቸው ወቅት ምንም አይነት ሀሳብ አለማንሳታቸውንም ቃል አቀባዩ ጠቁመዋል፡፡ በመግለጫው ሳማንታ ፓወር ኢትዮጵያ ከመምጣታቸዉ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩንና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማግኘት እንደሚፈልጉ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፤ በስራ መደራረብ ምክንያት ሊያገኟቸው እንደማይችሉ ተነግሯቸው ነበር ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *