loading
ሳውዲ በካሾጊ ግድያ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በሞት እንዲቀጡ ፍላጎት አለኝ አለች፡፡

አርትስ 07/03/2011
የሳዉዲ አረቢያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ግድያ እጃቸው አለበት ያላቸውን አምስት
ግለሰቦች በሞት መቀጣት አለባቸው ብሏል፡፡
ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ሳውድ ሞጂብ ተጠርጣሪዎቹ ካሾጊን በአደገኛ መድሀኒት መርፌ ወግተው
እንደገደሉት ተናግረዋል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው የካሾጊ አስከሬን በኬሚካል እንዲፈርስ ከተደረገ በኋላ ከተገደለበት የሳውዲ
ቆንስላ ፅህፈት ቤት እንዲወጣ ተደርጓል፡፡
ባለፈው ወር የቱርክ አቃቤ ህግ ጋዜጠኛው ኢስታምቡል በሚገኘው የሳውዲ ኢምባሲ እንደገባ ታፍኖ
ስለመገደሉ ተናግሮ ነበር፡፡
የሳውዲ መንግስት ከካሾጊ ግድ ጋር በተያያዘ 18 ሰዎችን ሲያስር አምስት ባለስልጣናትን ከስራቸው
አባርሯል፡፡
ቱርክ በበኩሏ ሳውዲ በግለሰቡ ግድያ የተጠረጠሩትን ግለሰቦችን አሳልፋ አደንድትሰጣት ጠይቃለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *