loading
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ጥራት ያለው የቴሌኮም አገልግሎት ለመሥጠት እየሰራሁ ነው አለ፡፡

አዲስ አበበ፣ የካቲት 16፣ 2014 ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ጥራት ያለው የቴሌኮም አገልግሎት ለመሥጠት እየሰራሁ ነው አለ፡፡ ኩባንያው ይህን የገለጸው በ100 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ያስገነባቸውን መሰረተ ልማቶችና የዳታ ቤዝ ማእከሉን ለጋዜጠኞች ባስጎበኘበት ወቅት ነው፡፡ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ጥራት ያለው የቴሌኮም አገልግሎት ለመሥጠት እየሰራ መሆኑን የኩባንያው የውጭ ጉዳይና የቁጥጥር ኦፊሰር ማቴ ሃሪሰን ሃርቬይ ተናግረዋል፡፡


ተቋሙ ጨረታውን ማሸነፉን ተከትሎ በኢትዮጵያ በዘርፉ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የቴሌኮም አገልግሎት ለመሥጠት የሚያስችለውን የቴክኖሎጂ ማሟያ ሥራ እያከናወነ መሆኑንም ገልጿል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለጋዜጠኞችና ለጎብኝዎች የሙከራ የድምጽ፣ የአጭር ጽሑፍ፣ እንዲሁም የዳታ ሙከራዎች አሁን ላይ በገነባቸው መሰረተ ልማቶች አማካኝነት መከናወኑን በተሳካ መልኩ አሳይቷል።

ከአምስት ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰራተኞችን ቀጥሮ እያሰራ የሚገኘው ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ በሚገባበት ወቅት ደግሞ የሰራተኞቹ ቁጥር በብዙ እጥፍ እንደሚጨምር በመግጫው ተነግሯል። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ የመረጃ ቋት ማዕከል የገነባ ሲሆን በሌሎች የክልል ከተሞችም ቀስ በቀስ የተደራሽነት አድማሱን እያሰፋ እንደሚሄድ ኩባንያው ገልጿል፡፡ ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ የተሰኘው ጥምረት የሚመራው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ850 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ አሸንፎ በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ መሰማራቱ ይታወሳል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *