loading
ሴሌሜ ሴሌሜ በሚለው የሀዲያኛ ሙዚቃ የሚታወቀው አርቲስት አቡሎ ጥሞሮ በ56 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አርትስ 17/03/2011

አርቲስት አቡሎ ጥሞሮ በሀዲይኛ ቋንቋ በርካታ ዜማዎችን ከ40 ዓመታት በላይ ተጫውቷል።

አርቲስት አቡሎ  በ11 ዓመቱ ሙዚቃ መጫወት መጀመሩ ይነገራል።

በተለይም አርቲስቱ በህዝብ ዘንድ በርካታ እውቅና ያስገኙለት ዜማዎች ለአድናቂዎቹ አድርሷል።

ከእነዚህ ዜማዎች መካከልም “ሴሌሜ ሴሌሜ ቦያ ሴሌሜ” የሚሰኘው ዜማ ከሀዲይኛ ቋንቋው ተናጋሪዎች ውጭ እውቅና አስገኝቶለታል።

አርቲስት አቡሎ ጥሞሮ በቅርቡ በጤናው ላይ በገጠመው እክል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትላንትና ምሽት  ማረፉ ተሰምቷል

አርቲስቱ ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበር።

አርትስ ቲቪ  ለአርቲስቱ ቤተሰቦቹና አድናቂዎች መጽናናትን ይመኛል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *