loading
ሴት አመራሮች የላቀ የአመራር ጥበብና በውሳኔ አሰጣጥ የተግባቦታዊ ኪሂል በመጎናፀፍ ተቋማቸውን በብቃት ሊመሩ እንደሚገባ ተገለፀ ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 03፣ 2013 ሴት አመራሮች የላቀ የአመራር ጥበብና በውሳኔ አሰጣጥ የተግባቦታዊ ኪሂል በመጎናፀፍ ተቋማቸውን በብቃት ሊመሩ እንደሚገባ ተገለፀ ፡፡ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከሁሉም የፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ሴት ሚኒስትሮች፣ ሴት ሚኒስቴር ዴኤታዎች፣ ሴት የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ ኮሚሽነሮችና በከፍተኛ ሴት አመራር ደረጃ ለሚገኙ አካላት የአመራር ጥበብና ተግባቦታዊ ክሂላቸውን የሚያዳብሩበት ስልጠናና እርስ በርሳቸው የካበተ ልምዳቸውን የሚያጋሩበት መድረክ በአዳማ ተካሂዷል፡፡

ስልጠናውን ያቀረቡት በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ የልማት ጥናት የጋዜጠኝነትና ተግባቦት መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር መልስው ደጀኔ እንደተናገሩት ሴት አመራሮች ከተቋማቸው ባሻገር እስከታችኛው ማህበረስ ድረስ ወርደው የሴቶችን ፍትሓዊ ተጠቃሚነትና የሚደርሱባቸውን በደሎች ጭቆናዎችን ለማስወገድ የዳበረ
የአመራር ጥበብና ተግባቦታዊ ኪሂላቸው የላቀ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

ሴት አመራሮች የሚፈልጉትን ግብ ለማስፈጸምና በውሳኔ አሰጣጥ ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ ሠራተኞችንና ህብረተሰቡን ለማሳመን በጽሁፍም ሆነ በንግግር የላቀ ክህሎት ሊኖራቸው እንደሚገባ ጠቅሰው ይህን ክህሎት ሳያዳብሩ በየደረጃው የሚገኙ መደበኛና ኢመደበኛ አደረጃጀቶችን በጥልቀት በመረዳት ተቋማትን ለመምራት እንደሚቸገሩ አብራረተዋል፡፡

ዶ/ር መልሰው አክለውም ትክክለኛ መሪ ለመሆን በተወከሉበት ተቋምና ህብረተሰብ ዘንድ መታመንና መከበር ቀዳሚ ተግባር መሆን እንዳለባቸው ተናግረው አመራሮች ራእያቸውን ለማሳካት ራሳቸውንና ተቋማቸውን ለመግለጽ በቂ ተግባቦታዊ ኪሂል ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *