loading
ስምንተኛዉ የበጎ ሰዉ ሽልማት መርሃግብር ጳጉሜ 1 ሊካሄድ ነዉ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13፣ 2012 ስምንተኛዉ የበጎ ሰዉ ሽልማት መርሃግብር ጳጉሜ 1 ሊካሄድ ነዉ፡፡ “በጎ ሰዎችን በማክበር እና እዉቅና በመስጠት ሌሎች በጎ ሰዎችን እናፈራለን” በሚል መረሃግብር በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን በአስር ዘርፎችም ለአገራቸዉ በሞያቸዉ የላቀ ተግባር ላበረከቱ ሰዎች ይበረከታል፡፡

የበጎ ሰዉ ሽልማት ድርጅት ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ የዘንድሮ የሽልማት መርሀግብር ከየካቲት 1 አስከ መጋቢት 15 ከ200 በላይ እጩዎችን ተቀብሎ ስራቸዉን ማጥናቱን ግን በኮቪድ ምክንያት የተሟላ ዝግጅት ማድረግ አለመቻሉን ገልጿል፡፡የበጎ ሰዉ ሽልማት ሥራ አመራር ቦርድም ሁኔታዉን ከግምት ዉስጥ በማስገባት የዘንድሮ ሽልማት መርሃግብር በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባት ስራ እንዲሳካና ለመጀመርያዉ ዉሃ ሙሌት እንዲበቃ ላደረጉ በጎ ሰዎችና ድርጅቶችን ለመዘከር የሚዉል ነዉ ተብሏል፡፡በተጨማሪም የኮሮናቫይረስ መከሰትን ተከትሎ አሰተዋጽኦ ያደረጉም ይመሰገኑበታል ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *