loading
ስምንት የግብጽ ወታደሮች በፀረ ሽብርተኝነት ተልዕኮ ላይ ሳሉ መገደላቸው ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 26፣ 2013 ስምንት የግብጽ ወታደሮች በፀረ ሽብርተኝነት ተልዕኮ ላይ ሳሉ መገደላቸው ተገለፀ፡፡ ስምንቱ ግብጻውያን ወታደሮች በጸረ ሽብርተኝነት ተልዕኮ በነበሩበት መገደላቸውን የጦሩ ቃል አቀባይ ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡ እንደ ወታደራዊ ሃይሉ መግለጫ በአብዛኛው ውጊያው እየተካሄደ የነበረው የታጠቁ የዳኢሽ ቡድኖች በሚንቀሳቀሱበት ሰሜናዊ ሲናይ በረሃ ላይ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ወታደሮቹ በሙሉ እዚያ ይሁን በሌላ ስፍራ ስለመሞታቸው ግን ምንም የተባለ ነገር የለም፡፡ በጦርነቱ ሰማኒያ ዘጠኝ ታጣቂዎች መገደላቸውንም የጠቀሰው የጦር ሃይሉ መግለጫ ታጣቂዎቹ ሙሉ ለሙሉ የአሸባሪው ቅጥረኞች መሆናቸውን ያነሳል፡፡ ወታደራዊ ሃይሉ በአሸባሪዎቹ ላይ የተለያዩ ከባድ መሳሪያዎችን አንስቶ የአየር ድብደባ ድረስ መፈጸሙን አስታውቋል፡፡

በጥቃቱም በጋዛ ሰርጥና በእስራኤል ድንበር የሚገኙ በርካታ ምሽጎችን መደምሰሱም ተገልጿል፡፡ ጥቃቱ መቼ በውል እንተደፈጸመ የተባለ ነገር አለመኖሩን ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *