ስፔን ከሳውዲ ጋር የመሳሪያ ሽያጭ ውሌን አፍርሻለሁ አለች፡፡
አርትስ 29/12/2010
የስፔኑ ጋዜጣ ኤልዲያሪዮ እንደዘገበው በማድሪድና በሪያድ መካከል የ10.6 ሚሊዮን ዶላር የመሳሪያ ሽያጭና ግዥ ውል ተፈርሞ ነበር፡፡
ውሉ የተፈረመው በቀድሞው የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ራሆይ ሲሆን ስፔን ውሉን ለማፍረስ ምክንያት የሆናት ሳውዲ አረቢያ በየመን ባካሄደችው የአየር ትቃት በርካታ ህጻናት መሞታቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡
ሳውዲ 400 የሚሆኑ ከፍተኛ ሀይል ያላቸው ቦምቦችን ከስፔን ልትገዛ የነበረ ቢሆንም ስምምነቱ በአዲሱ አስተዳር ተሰርዟል፡፡
የስፔን መንግሰት ከዚህ በኋላ የሚደረጉ የመሳሪያ ሽያጮች ገዥው አካል መሳሪያዎቹን በሌላ ሀገር ላይ እንዳይጠቀምባቸው የሚከለክል ውል ያካተቱ መሆን አለባቸው ብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የትኛውም ሀገር ለሳውዲ አረቢያ መሳሪያ እንዳይሸጥ ግፊት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡