ሶልቭ ኢት የተባለዉ የፕሮጀክት መተግበሪያ ሀሳብ ያላቸዉን ወጣቶች ለማበረታታትና ለወጣቶች እድልን ለማመቻቸት ያለመ መሆኑ ተገለፀ፡፡
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2012 በአንድ ሀገር የሰላም እጦት ሁነት ሲበዛ ብዙ ምስቅልቅሎች ይፈጠራሉ፡፡ የአብዛኞቹ የሰላም እጦት መነሻ ደግሞ ከወጣቶች የስራ አጥነት ጋር ይያያዛል ፡፡የኢትዮጵያም ከዚህ የተለየ አይደለም ፡፡በኢትዮጵያም የስራ አጥነት ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቶ አሁን ላይ የተማረዉ ያልተማረዉም ወጣት ስራ አጥ መሆኑ የተለመደ ሆኗል፡፡ታዲያ ችግሩን ለመቅረፍ ጥረቶች ቢደረጉም ከችግሩ ስፋት አንጻር ለወጣቶች የስራ እድልን በስፍት መፍጠር አልተቻለም፡፡አሁን ለወጣቶች ስራ እድል የመፍጠሩ ጉዳይ ለመንግስት ብቻ የሚተዉ ባለመሆኑ የግልና በጎአድራጎት ተቋማትም በተለይ ስራ ፈጣሪ የሆኑና ለሌሎች የስራ እድል ለሚፈጥሩ ወጣቶች የገንዘብና የሞያ ድጋፍ እያደረጉ ነዉ፡፡ከነዚህ ደግሞ አንዱ ሶልቭ ኢት ፕሮጀክት መተግበሪያ ነዉ፡፡
መተግበሪያዉ ማህበራዊ ችግሮችን መፍታት ላይ ያተኮረ የቢዚነስ ሀሳብ ያላቸዉ ወጣቶችን አወዳድሮ የሚሸልም ሲሆን ፡በኢትዮጵያ ለ3ተኛ ጊዜ ነዉ ይፋ የተደረገዉ፡፡በአሜሪካ ኤምባሲ እንዲሁም በጂአይካ ድጋፍ የሚደርግለት ይህ ፕሮጀክት፡ ከመንግስት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ፡የፌደራል አነስተኛና መካከለኛ ማኒፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማስፋፍያ ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር አቶ አስፋዉ አበበ መስራያ ቤቱ ለአሸናፌዎች ቦታ ከማመቻቸትና አቅማቸዉን የመገንባት ድርሻ እንዳለዉ ነዉ ያብራሩት ፡፡የፕሬጀክቱ ዉድድር ላይ ለመሳተፍ እስካሁን በአ.አ 500 በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከ200ሺ በላይ ሰዎች ተመዝግበዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በባህር ዳር ፕሮጀክቱ ተተግብሮ ዉጤታማ እንደሆነ የነገሩን የፕሮጀክቱ ማናጀር ፡በሀገሪቱ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማሳደግና ወጣቶችን ለመደገፍ አጋጣሚዉ መልካም እንደሆነ ነዉ የገለፁልን ፡፡