loading
ሶማሊያ ሞቃዲሾ ከተማ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 17 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸው ተሰምቷል::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 11፣ 2012 ሶማሊያ ሞቃዲሾ ከተማ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 17 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸው ተሰምቷል:: የሀገሪቱ መንግስት ቃል አቀባይ ኢስማኤል ሙክታር ኦማር እንዳሉት ጉዳቱ የደረሰው የአልሸባብ ታጣቂዎች በአንድ ሆቴል በከፈቱት ጥቃት ነው፡፡ ቃል አቀባዩ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ጥቃቱን ያደረሱት አራቱም የአልሸባብ ታጣቂዎች በተኩስ ልውውጡ ወቅት በመንግስት የፀጥታ ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ከሶስት ሰዓታት በላይ በፈጀው የተኩስ ልውውጥ የተጀመረው በመኪና ላይ የተጠመደ ቦንብ በማፈንዳት እንደነበር አሶሼትድ ፕሬስ በዘገባው አስነብቧል፡፡

ከሞቱት 17 ሰዎች በተጨማሪ 28 የቆሰሉ ሰዎንች ወደ ሆስፒታል ማጓጓዛቸውን የአምቡላንስ ሰራተኞች ተናግረዋል፡፡ ከቆሰሉት ሰዎች መካከል ሁለት የመንግስት ሰራተኞች፣ ሶስት የሆቴሉ የጥበቃ አባላት እና አራት ሲቪል ሰዎች ይገኙበታል፡፡ አልሸባብ ለደረሰው ጥቃት ሙሉ በሙሉ ሀላፊነቱን እንደሚወስድ የሚገልፅ መረጃ ማሰራጨቱን የሞቃዲሾ የደህንት ሰዎች ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት በማእከላዊ ሞቃዲሾ ባለ አንድ እስር ቤት የሚገኙ የአልሸባብ አባላት ከእስር ቤቱ የጥበቃ አባላት ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርገው በመጨረሻ መገደላቸው ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *