loading
ሶማሊያ አስከፊ የተባለውን እስር ቤቷን ዘጋች

አርትስ 08/04/2011

የሶማሊያ የጸጥታ ሚኒስትር አህመድ አቡካር እንደገለጹት አገሪቱ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይካሄድበት የነበረውን   አንደር ግራውንድ እስር ቤት ዘግታ ለሌላ ተግባር አውላዋለች፡፡

ይህ ኮድካ ጂላዎ በመባል የሚታወቀው እስር ቤት  በተለይም ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ የሽብር ተጠርጣሪዎች የሚታሰሩበት እንደሆነ ይነገራል፡፡

በመቶዎች የሚቆጠሩ ታራሚዎችም  በእስር ቤቱ ይገኛሉ፡፡

ይህ እስር ቤት በጋዜጠኞች እና በሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች  ተቃውሞ ሲነሳበት እንደነበረ  ነው የፀጥታ ሚኒስትሩ የገለፁት፡፡

የእስር ቤቱ መዘጋት የሃገሪቱን የሰብአዊ መብት አያያዝ መዝገብ ለማሻሻል ያለመ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም  በእስር ቤቱ የነበሩ እስረኞች  ወደ ሌላ ቦታ ተዘዋውረው  ወደ ቴክኒክ ትምህርት ቤትነት ተቀይሮ በርካቶችን ተጠቃሚ ያደርጋል ኒውስ 24 እንደዘገበው ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *