loading
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ከኃላፊነቴ የምለቀው በሱልልታ የአገር አቋራጭ ውድድር አትሌቶች ባነሱት ቅሬታ ነው አለ

አርትስ 03/03/2011
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነት የለቀቀው በገዛ ፍቃዱ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ፌዴሬሽኑን ባለፉት ሁለት አመታት በፕሬዚዳንትነት ሲመራ የቆዬ ሲሆን፤ በአትሌቲክሱ ጠፍቶ የነበረው ውጤት እንዲመለስ የበኩሉን ሲወጣ ነበር፤ በቅርቡ ከአትሌቶች እና አሰልጣኞች ማህበር በኩል ፌደሬሽኑ ላይ ስሞታ ሲቀርቡበት እንደነበርም ይታወሳል፡፡ ኃይሌ ገብረስላሴ ባስገባው የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ በተለያዩ ወቅቶች የፌዴሬሽኑን የአሰራር ችግሮችን አንዳንድ ግለሰቦች፤ ትልቅ ተቋማትን መከታ አድርገው የፌዴሬሽኑንና የዓለም ዓቀፍ አትሌቲክስ መርሆዎችን ለማስቀልበስ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል ብሏል፡፡ በትላንትናው ዕለትም በሱልልታ የአገር አቋራጭ ውድድር በየትም ዓለም የማይፈፀም ድርጊት ኢንዲፈፀም ሁኗል፤ ሀገርን ወክለው ከፍተኛ ቦታ የሚደርሱ ባለ ራዕዮችንም፤ ለግል ጥቅማቸው መጠቀሚያ አውለዋቼዋል ሲል ማዘኑን አስፍሯል፡፡ ኃይሌ ገብረስላሴ ይህ አይነት ድርጊት ለአትሌቲክሱ የማይበጅ መሆኑን አስቀድሞ ቢረዱም ቀስ በቀስ ሊሻሻል ይችላል በሚል በትዕግስት እንደጠበቀና ነገር ግን የትናንቱ ድረጊት ቅጣት የሚያስከትል በመሆኑና አተካሮ ውስጥ ከመግባት ከተሰጠው ኃላፊነት መልቀቁ ተገቢ መሆኑን በማመኑ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ በእርሱ ቦታ የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ በአስቸኳይ ስብሰባ እስኪገናኝ ድረስ በጊዜያዊነት የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኮልኔል ደራርቱ ቱሉ እርሱን ተክታ እንደምትሰራ አስታውቋል፡፡ በላፊነት በነበረበት ጊዜ ከጎኑ ለነበሩት አካላትም ምስጋና አቅርቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *