loading
በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት አግባብ አይደለም-¬ቻይና፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11፣ 2013 ኢትዮጵያ ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት የውጭ ጣልቃ ገብነት እንደማያስፈልጋት ቻይና ገለጸች፡፡

አምባሳደር መለስ ዓለም በኬንያ ከቻይና አምባሳደር ዦ ፒንጂያን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

በዚሁ ወቅት አምባሳደሩ በአገሮች የውስጥ ጉዳይ የሚደረግ ጣልቃ ገብነት ቻይና እንደምትቃወም ተናግረዋል።

የውስጥ ጉዳይ የየአገራቱ ኃላፊነት በመሆኑ ሌሎች አገሮች በተናጥል ጣልቃ መግባት እንደሌለባቸው አምባሳደር ፒንጂያን ገልፀዋል።

ቻይና ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብቶችን ከግርጌ አገሮች ጋር በትብብር የመጠቀም ልምድ እንዳላት የተናገሩት አምባሳደር ፒንጂያን ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱ አገራቸው እንደምትደግፍ አረጋግጠዋል።

ቻይና ሶስቱ ሀገራት የገቡበትን ውዝግብ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ በሚለው መርህ መፍታት አለባቸው የሚለውን አቋሟን በተደጋጋሚ ስትገልፅ ቆይታለች፡፡

ሰሞኑን መግለጫ ያወጣውን የአረብ ሊግን ጨምሮ አንዳንድ ሀገራት ጉዳዩን ሌሎች አሸማጋዮች ይግቡበት የሚለውን ሀሳብ የኢትዮጵያ ወዳጆች እየተቃሙት ይገኛሉ::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *