loading
በሀገራችን ያለውን የአይን ህክምና ዘርፍ ከፍ የሚያረግ እና የተሻለ ህክምና የሚገኝበት ላቪስታ የአይን ህክምና ክሊኒክ ተመርቆ ስራ ጀመረ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 6 ፣ 2013 በሀገራችን ያለውን የአይን ህክምና ዘርፍ ከፍ የሚያረግ እና የተሻለ ህክምና የሚገኝበት ላቪስታ የአይን ህክምና ክሊኒክ ተመርቆ ስራ ጀመረ:: ላቪስታ የአይን ህክምና በሀገራችን ያለውን የአይን ህክምና ዘርፍ ለማገዝና በተሻለ ለመስራት መቋቋሙ ተነግሯል፡፡ እንዲሁም በአዳዲስ የአይን ህክምና መሳሪያዎች በመታገዝ ታካሚዎች የተሻሉ የተባሉ መሳሪያዎች ለማግኘት ወደ ውጪ ሀገር ሄደው ለመታከም የሚገደዱበትን ዘመናዊ ህክምና ለማስቀረትና ዜጎች በአገራቸው በትንሽ ወጪ አገልግሎቱን ለማግኘት እንዲችሉ የተመሰረተ ማዕከልነው ተብሏል ።

የላቪስታ የአይን ህክምና በለቤት የሆኑት ዶ/ር ሳዲን ሀይሉ በምረቃ ስነስርአቱ ላይ ባሰሙት ንግግር ጥሩ የሆነ የህክምና ባለሙያ ዘመናዊ የሆነ የህክምና መስጫ መሳሪየ ከላገኘ ውጤትን ሊያመጣ አይችልም ብለዋል፡፡ላቪስታ ይሄን ለመቅረፍ ጥሩ ባለሙያና ዘመናዊ መሳሪየን በመጠቀም የታካሚዎችንችግር ለመፍታት
የተቋቋመ የህክምና ማዕከል ነው በማለት ተናግረዋል።

የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ድጉመ በበኩላቸው የጤና አገልግሎት ጥራት ላይ ለመስራት በምንጥርበት በዚህ ወቅት የላቪስታ የአይን ህክምና መአከል ጥራትን ከዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች እና በዘርፉ ከሰለጠኑ የህክምና በለሙየዎች ጋር በማጣመር የሚፈለግበትን አገልግሎት ለዜጎች መስጠት በመጀመሩ ሊበረታታ ይገባል ብለዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *