loading
በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋር የነበረ ብርድልብስ በቁጥጥር ሥር ዋለ፡፡

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋር የነበረ ብርድልብስ በቁጥጥር ሥር ዋለ፡፡

በትላንትናዉ  ዕለት ግምታዊ ዋጋው 200ሺህ ብር የሆነ ህገ-ወጥ ብርድልብስ በቁጥጥር ሥር መዋሉን በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ቅ/ጽ/ቤቱ እንደገለጸው፤ ጥር 19/2011 ዓ.ም ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት የሰሌዳ ቁጥሩ 57675 ኦሮ የሆነ ተሽከርካሪ ከጅግጅጋ ወደ ሀረር በመጓጓዝ ላይ እንዳለ በጉምሩክና በክልሉ አድማ ብተና አካላት በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡

የመኪና አሽከርካሪው ለጊዜው ስላመለጠ ቅ/ጽ/ቤቱ ክትትል እያደረገ ሲሆን ማህበረሰቡም ለሕግ በማቅረብ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ምንጭ ፤-ገቢዎች ሚኒስቴር

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *