በህጋዊ ሽፋን የሚደረግ ህገወጥ የሥራ ጉዞ ከዛሬ ጀምሮ ይታገዳል
በህጋዊ ሽፋን የሚደረግ ህገወጥ የሥራ ጉዞ ከዛሬ ጀምሮ ይታገዳል
የሥራ ስምሪት ባልተፈቀደባቸው በመካከለኛው ምስራቅ አገራት ህጋዊ በሚመስል መንገድ ለሥራ እየተጓዙ የሚገኙ ዜጎችን ከሚደርስባቸው እንግልትና ስቃይ ለመታደግ ከዛሬ ጀምሮ ክትትልና ቁጥጥርበማድረግ የማገድ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የተቋቋመው ሀገር አቀፍ ግብረ ኃይል ሰሞኑን ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ባካሄደበት ወቅት ቁጥጥርና ክትትል ይደረጋል ያለው፡፡
አስቀድሞም ለፌደራል ፖሊስ፣ ለሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ለኢምግሬሽንና የዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ፣ ለኢትዮ ጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን እና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ትዕዛዝማስተላለፉን አስታውሷል፡፡
በህጋዊ መንገድ ለሥራ የሚጓዙ ዜጎች የተለያዩ ሙያ ሥልጠናዎችን፣ የብቃት ማረጋገጫና የቅድመ ጉዞ ሥልጠና ይወስዳሉ ፤ እንዲሁም መታወቂያ ይሰጣቸዋል፣ የሥራ ውልም ይፈራረማሉ ፡፡ ይህንን ሂደትያላሟሉ ተጓዦች ህጋዊ በሚመስል መንገድ ሲንቀሳቀሱ ከተገኙ ከዛሬ ጀምሮ ይታገዳሉ፡፡
ከሳዑዲ አረቢያ፣ ከጆርዳን እና ኳታር ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት የተፈረመ ሲሆን ፤ ከዩናይትድ አረብ ኤምሬት፣ ቤይሩት፣ ኩዌት፣ ባህሪንና ኦማን ጋርም የሁለትዮሽ ስምምነት ለማድረግ በሂደት ላይ መሆኑንሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለ ኢዜአ አስታውቋል፡፡
ዜጎች ህጋዊ በሚመስል መንገድ የሥራ ስምምነት ወዳልተደረገባቸው አገራት የቱሪስት፣ የዘመድ ጥየቃ፣ የጉብኝት፣ የንግድና የመሳሰሉትን የቪዛ ዓይነቶችን ይዘው በብዛት ከአገር እየወጡ ይገኛሉ ብሏል፡፡
በዚህ መንገድ ተጉዘው ሥራ የሚቀጠሩ ዜጎች ህጋዊ አለመሆናቸውን በመረዳትና ቪዛው የሚያገለግለው ለአጭር ጊዜ በመሆኑ አካሄዳቸውን እንዲያስተካክሉ ያሳሰበው መስሪያ ቤቱ ህግን ባልተከተለመንገድ ስምምነት ወዳልተደረገባቸው አገራት የሚጓዙ ዜጎች በቀን እስከ 1ሺ300 ይደርሳሉ ብሏል፡፡