loading
በላሊበላ ከተማ በመጭው እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ ሊካሄድ ነው

አርትስ 25/01/2011

የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ላይ የተሰሩ መጠለያዎች ቅርሱን እየጎዱት በመሆኑ ቅርሱን እናድን በሚል የከተማዋ ነዋሪዎች በመጪው እሁድ ከ ጠዋቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚወጡ አርትስ ለማወቅ ችሏል፡፡

የላሊበላን ውቅር አብያተክርስቲያናት ከዝናብና ፀሐይ ለመታደግ በጊዜያዊነት የተሰራው መጠለያ ቅርሶቹ ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጦ መጠለያውንም አንስቶ ለመጠገን 300 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ የተገለፀ ቢሆንም ወደ ተግባር ለመግባት ዘግይቷል ሲሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ለአርትስ ቲቪ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *